ግብር ያልከፈሉ 62 ሰዎች ላይ የጉዞ እገዳ መጣሉ
ዓርብ፣ የካቲት 28 2017
62 የግብር እዳ ያለባቸዉ ሰዎች የጉዞ እገዳ ተጣለባቸዉ
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ከ3 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ የሚሆን የግብር እዳ አለባቸው ባላቸው 62 ግብር ከፋዮች ላይ የጉዞ እገዳ መጣሉን አስታወቀ። የገቢዎች ቢሮ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሰውነት አየለ ዛሬ የካቲት 28 ቀን 2017 ለዶቺቪሌ በሰጡጥ ቃለ-ምልልስ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ 3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ የታክስ ዕዳ ያለባቸው 62 ግብር ከፋዮች የግብር ገንዘብ ይዘው እንዳይሰወሩ በሚል ነው፤ ከሀገር እንዳይወጡ የእገዳ ውሳኔ የተላለፈባቸው። እገዳው የተጣልባቸው የግለሰቦች ያለባቸውን የግብር እዳ እንዲከፍሉ ቤሮው በተድጋጋሚ በተላያየ መንገድ ያደረገን ጠሪ ተቀብለው ግብር ለመክፈል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ነው ብለዋል።
አቶ ሰውነት አየለ ቤሮዋቸው ይህንን የግብር እዳ ለመሰብሰብ ከሁለት አመት በላይ ሙከራ ሲያደርግ መቆየቱን ገልፀው ነገር ግን እነኝህ 62 ግለሰቦች ለከተማዋ ልማት የሚውል ነው የተባለውን ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ የግብር ዕዳ ለመክፈል ፍቃደኛ ሆነው ባለመገኘታቸው የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በታክስ አስተዳደር አዋጅ መሰረት ነው ከሀገር እንዳይወጡ እገዳ ያስተላለፈባቸው።በኢትዮጵያ የንብረት ታክስ ማን ስንት ይከፍላል?
በትላንትናው እለት ይፋ የሆነው መግለጫ የግለሰቦቹ ስም ከሀገር እንዳይወጡ ለኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መተላለፉን እና አሁን የባለእዳዎቹ ቋሚ እና ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን የማፈላለግ ስራ እንደ ሚጀመር የተናገሩት አቶ ሰውነት ፤ባለፈው ዓመት ብቻ ከ 11 ቢልየን ብር በላይ ያልተከፈለ የግብር እንዳ እንደነበረ ተናግረው የከተማ አስተዳደሩ የዕዳ ክትትልና አስተዳደር የስራ ክፍልን በአዲስ መልክ በማደራጀት ወደ ስራ በመግባቱ ከ6 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ዕዳ መሰብሰቡን ገልፀዋል፡፡
ህግ ባለሙያው አቶ የወግሰው በቀለ( ጠበቃ እና የሀግ አማካሪ) ለዶቺ ቬሌ፤ እንደገልፁት የገቢዎች አንድን ሰው ከሀገር እንዳይወጣ የሚያግድበት ምክንያት ግለሰቡ ያልከፈለውን የግብር እዳ ማስከፈል ያስችለው እንደሆነ ነው ሲሉ ገልፀዋል። የአዲስ አበባ ገቢዎች ቤሮው ከተማዋ ለምታደርገው ልማት ገቢ ማሰባሰብ እንደሚሰራ የገልፁት አቶ ሰውነት በ2017 የበጀት ዓመት በከተማዋ ከሚደረገው የንግድ እንቅስቃሴ ከ 230,4 ቢልየን ብር በላይ ግብር ለመሰብሰብ እቅድ እንደተይዘ ገልፅዋል።
ሃና ደምሴ
አዜብ ታደሰ
ታምራት ዲንሳ