ግንዛቤ የሚያሻዉ የስጋ ደዌ
ማክሰኞ፣ የካቲት 16 2002ማስታወቂያ
የዛሬ 55ዓመት ዕለቱ ታስቦ እንዲዉል ሲታሰብ በደዌዉ ተጠቂዎች ላይ በየደረጃዉ የሚደርሰዉን መገለል ለማስቀረት፤ እንዲሁም በኅብረተሰቡ ዘንድም ስለበሽታዉ ያለዉን ግንዛቤ በማስፋት መብታቸዉን ማስጠበቅ ታልሞ ነዉ። ዛሬም ግን በሌላዉ ኅብረተሰብ ዘንድ ስለበሽታዉና ታክሞ መዳን ስለመቻሉ ያን ያህል ግንዛቤ ባለመኖሩ ተጨባጭ ባልሆኑ ምክንያቶች የስጋ ደዌ ተጠቂዎች ኑሮ ቀላል የሚባል አልሆነም። ዕለቱ በያዝነዉ ሳምንት ማለቂያ ዘንድሮ በኢትዮጵያ በብሄራዊ ደረጃ ለ11ኛ ጊዜ ታስቦ ይዉላል። በአገሪቱ በየዓመቱ ወደአምስት ሺ የሚሆኑ አዳዲስ የበሽታዉ ተጠቂዎች እንደሚገኙ ይነገራል።
ሸዋዬ ለገሠ ሂሩት መለሰ