1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ግዕዝ ቋንቋ በአማራ ክልል ስርአተ ትምህርት መካተት ያስነሳዉ ተቃዉሞ

ኢሳያስ ገላው
ሰኞ፣ መስከረም 5 2018

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ጥንታዊ የግእዝ ቋንቋን በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲማሩ መወሰኑን የተቃወሙ የእስልምና ሀይማኖት መሪዎች ዉሳኔዉ ቋንቋዉን ለማስተማር ሳይሆን የሌሎች እምነትን ባህልና እሴት ለማስተማር ነዉ ሲሉ የደሴ ከተማና ኮምቦልቻ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ቅሬታቸዉን በደብዳቤ ለአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አቅርበዋል።

የግዕዝ ቋንቋ ጽሑፍ
የግዕዝ ቋንቋ ጽሑፍ ምስል፦ CPA Media Co. Ltd/picture alliance

ግዕዝ ቋንቋ በአማራ ክልል ስርአተ ትምህርት መካተት ያስነሳዉ ተቃዉሞ

This browser does not support the audio element.

ግዕዝ ቋንቋ በአማራ ክልል ስርአተ ትምህርት መካተት ያስነሳዉ ተቃዉሞ 

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ጥንታዊ የግእዝ ቋንቋን በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲማሩ መወሰኑን የተቃወሙ የእስልምና ሀይማኖት መሪዎች  ዉሳኔዉ ቋንቋዉን  ለማስተማር ሳይሆን የሌሎች እምነትን ባህልና እሴት ለማስተማር ነዉ ሲሉ የደሴ ከተማና ኮምቦልቻ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ቅሬታቸዉን በደብዳቤ ለአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አቅርበዋል። የግዕዝ ትምህርት በቶሮንቶ ዩንቨርሲቲ

በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በአዲሱ የትምህርት ዘመን የግዕዝ ቋንቋ ትምህርትን በ1ኛ እና በመካከለኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ከ3ኛ ክፍል ጀምሮ እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት እንዲሰጥ መወሰኑን እንቃወማለን ያሉ የደሴ ኮምቦልቻ እናደቡብ ወሎ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤቶች ቅሬታቸውን ለክልሉ ትምህርት ቢሮ አቀረቡ፡፡ አስተያየታቸውን ለዶቼቬ ለየሰጡት የኮምቦልቻ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት የምሁራን ተጠሪ የሆኑት አቶ አሊ ሰይድ የግዕዝ ትምህርትን ጥንታዊነት ጠቅሰው የግዕዝን ትምህርት ለአለማዊ ትምህርት ለማዋል በርካታ መሻሻሎች ያስፈልጉታል ይላሉ፡፡ ‹‹አሁን ወደ አለማዊ ትምህርት ስርዓት ማምጣት ከተፈለገ ቋንቋው ብዙ መሻሻሎች ያስፈልጉታል ብዙ የሚሰሩ ቅድመ ሁኔታዎች መኖርም አለባቸው፡፡በቀጥታ ግዕዝን ወደአለማዊ ትምህርት ብናመጣው መንፈሳዊ ገጽታውን ይዞነው የሚመጣው ከዚህ ጋር ተያይዞ የእስልምና እምነት ተከታዮች ለመማር ይቸገራሉ፡፡›› የግዕዝ ትምህርት በአማራ ክልል በስርአተ ትምህርቱ ዉስጥ መካተቱ ተቃዉሞ ገጠመዉ። የግእዝ ቋንቋን የማስመዝገብ ጥረት

ለማስተማሪያነት የተዘጋጁት መጽሐፍቶች የሐይማኖታዊ ይዘት ያላቸው ናቸው የየሚሉት የደሴ ከተማ እስልምና ጉዳዮችምክር ቤት ዋና ፀሀፊ አቶ ኡስማን ሁሴን የግዕዝ ቋንቋ ትምህርት ከ3ኛ ክፍል ከመጀመር ይልቅ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ቢገደብ የሚል አስተያየት ይሰጣሉ፡፡  ‹‹መጽሐፍቶቹ አብዝሃኛው ትርጉም ከእምነቱ ጋር የተያያዙናቸው፡፡ ይህንን ትምህርት ደግሞ ልጆቻች ንሊማሩ አይገባም የሚል ጥያቄ አለ፡፡ ትምህርቱ አይሰጥም ሲባል በዩኒቨርስቲ ደረጃ እየተሠጠ ነው፤ ለምርምር እና ጥናት ያንን አልተቃወ ምንም፤ ህፃናት ላይ ግን ይህ ትምህርት ሊሰጥ አይገባም፡፡›› 

 የደሴና ኮምቦልቻ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤቶች ደብዳቤ ፅፈዋል 

የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤቶች ያቀረቧቸው ጥያቄዎችሀይማኖትን ከመጠበቅ አንፃር እና በትምህርት ላይ ሀይማኖትተፅዕኖ ሊያደርግ አይገባም በማለት ነው ይላሉ አቶ አሊ ሰይድ፡፡ ‹‹ሀይማኖትን ከመጠበቅ አለማዊነትን ከማስጠበቅ አንፃርትምህርት ቤት ውስጥ የሚሰጡ ትምህርቶችንከሀይማኖትነክ ትምህርቶች ያገለሉ መሆን አለባቸው ሲል  ነው ጥያቄያቀረበው፡፡›› ለግዕዝ ቋንቋ ፍቅር ያደረባቸው ወጣቶች

2017 ዓም የግዕዝ ቋንቋ ትምህርት በክልሉ ተሰጥቶል

በ2017 ዓ/ም የግዕዝ ቋንቋ ትምህርትን የአማራ ክልል ትምህርትቢሮ በ16 ዞኖች በተመረጡ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ሲሰጥ ቆይቷል፡፤ ትምህርቱ ከተሰጠባቸው ወረዳዎች መካከል ደግሞ የአማራ ሳይነት ወረዳ አንዱ ነው፡፡ በሙከራ ደረጃም በ 2 ት/ቤቶች የግዕዝ ቋንቋ ትምህርት መሰጠቱን የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ትዕዛዙ አድማሱ ይገልፃሉ፡፡ ‹‹እንደ ወረዳ 2 ት/ቤቶች ላይ ለመስጠት በማኔጅመንት ወስነን ተድባበ ማርያም እና አጅባር 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እነሱን መርጠን መምህር ቀጥረን አስተምረናል፡፡›› የደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መመሪያ ሃላፊ አቶ አለምነው አበራ የግዕዝ ትምህርትን በባለፈው ዓመት ፈቃደኛ በሆኑ 7 ወረዳዎች ላይ የተሰጠ መሆኑን ገልፀው አሁን ማህበረሰቡያነሳውን ጥያቄ ለክልሉ መንግስት አሳውቀናል ብለዋል፡፡ ‹‹ሥርዓተ ትምህርት የመቅረፅ መብት የማህበረሰብ ሳይሆንየክልሉ ትምህርት ቢሮ ነው፡፡ ግዕዝ አለ ወይስ ሞቷል? ዞንና ወረዳየተሰጠንንሥርዓተ ትምህርት መተግበር ነው እንጂ መቅረፅ አንችልም፤ ማህበረሰቡ ያነሳውን ጥያቄም ለክልሉ መንግስት አቅርበናል፡፡›› የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ሃላፊ የሆኑት እየሩስ መንግስቱ አሁን በግዕዝ ቋንቋ ትምህርት አሰጣጥ ዙሪያ ማህበረሰቡ እያነሳ ያለውን ቅሬታ በተመለከተ በቅርቡ መግለጫ እንሰጣለን ብለዋል፡፡ 

ኢሳያስ ገላዉ 

አዜብ ታደሰ 

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሔር

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW