ግድያ በዩናይትድ ስቴትስ አሪዞና2 ጥር 2003ሰኞ፣ ጥር 2 2003በዩናይትድ ስቴትስ አሪዞና ግዛት ውስጥ ቅዳሜ ታህሳስ 30 በተፈፀመ የተኩስ ጥቃት 14 ሰዎች በፅኑ ሲቆስሉ 6 ሰዎች ደግሞ ሞቱ። በፀና ከቆሰሉት መካከል የአሜሪካ ምክር ቤት አባሏ ጋብሪዬል ጊፎርድስ ከፍተኛ ቀዶ ጥገና እየተደረገላቸው መሆኑም ታውቋል። እንደራሴዋ በጥይት የተመቱት ጭንቅላታቸው ላይ ነው።ማገናኛዉን ኮፒ አድርግጭንቅላታቸውን በጥይት የተመቱት የህዝብ እንደራሴ፣ ገብርኤል ጊፈርድ፣ምስል dapdማስታወቂያፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ክስተቱ ለግዛቷም ሆነ ለሀገሪቷ እጅግ አሳዛኝ መሆኑን ጠቁመዋል። ዝርዝሩን አበበ ፈለቀ ከዋሽንግተን እንደሚከተለው አጠናቅሮ ልኮልናል።