ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በበርሊን ተቃዉሞ ገጠማቸው
እሑድ፣ ኅዳር 9 2016ማስታወቂያ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ መሪዎች የሚሳተፉበት የቡድን 20 “ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ” ጉባኤ ነገ ሰኞ በበርሊን ከተማ ይካሔዳል። በጀርመን አዘጋጅነት በሚካሔደው ጉባኤ ከአፍሪካውያን መሪዎች በተጨማሪ የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝደንት ኡርሱላ ፎን ደርላየን፣ የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኤማኑዌል ማክሮ የኔዘርላንድስ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩተ ይሳተፋሉ።
“ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ” በጎርጎሮሳዊው 2017 ጀርመን የቡድን 20 ፕሬዝደንት ሳለች የተጀመረ ነው። ጉባኤው ለውጥ ፈላጊ የአፍሪካ ሀገራትን፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን እና አጋሮችን በማሰባሰብ የልማት ጉዳዮችን የማስተባበር እና በኢንቨስትመንት ላይ ለመወያየት የተወጠነ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በጉባኤው ለመሳተፍ በርሊን ሲደርሱ የጀርመን መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልስ ተቀብለዋቸዋል። ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በርሊን ሲደርሱ ጀርመን በሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዉያን ብርቱ ተቃዉሞ ገጥሟቸዋል።
ሙሉ ዘገባውን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።
ይልማ ሀይለሚካኤል
ፀሀይ ጫኔ