ጠቅላይ ምኒስትር አብደላ ሐምዶክ በፈረንሳይ
ማክሰኞ፣ መስከረም 20 2012
ማስታወቂያ
የሱዳኑ ጠቅላይ ምኒስትር አብደላ ሐምዶክ በፈረንሳይ ጉብኝታቸው ከዳርፉር አማጽያን መሪ አብዱዋሒድ ኑር ጋር ተገናኙ። ለ30 ደቂቃ ብቻ የታቀደው የጠቅላይ ምኒስትር አብደላ ሐምዶክ እና የአማፂያኑ ውይይት ለሦስት ሰዓታት ገደማ ዘልቋል። ሐምዶክ አብዱዋሒድ ኑር ጋር ስለ ሱዳን ቀውስ ሥረ- መሰረት እና መፍትሔዎቹ መነጋገራቸውን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
ጠቅላይ ምኒስትሩ አገራቸውን እንዲጎበኙ የጋበዙት ፕሬዝዳንት ኤማኑዌል ማክሮ ሐምዶክ ከአብዱላሒ ኑር ጋር ተገናኝተው እንዲወያዩ መንግሥታቸው ማመቻቸቱን ተናግረዋል። በስደት ኑሯቸውን ፈረንሳይ ያደረጉት አብዱዋሒድ ኑር የሚመሩት የሱዳን ነፃ አውጪ ጦር (SLA/AW) ለጠቅላይ ምኒስትር አብደላ ሐምዶክ መንግሥት እውቅና አልሰጠም።
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ መሠረት ለረዥም ዓመታት በዘለቀው የዳርፉር ቀውስ በአስር ሺሕዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል፤ ሁለት ሚሊዮን ገደማ ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል። ሐይማኖት ጥሩነህ የሱዳኑ ጠቅላይ ምኒስትር በፈረንሳይ ስለነበራቸው ጉብኝት ዘገባ አጠናቅራለች።
ሃይማኖት ጥሩነህ
እሸቴ በቀለ
አዜብ ታደሰ