1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ጋር ትወያዩ

ሰኞ፣ ሐምሌ 15 2016

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር በጽ/ቤታቸው ተወያዩ። በውይይቱ የተሳተፉ አንድ ፖለቲከኛ የሰላም፣ የፀጥታ፣ የሕገ መንግሥት፣ የኢኮኖሚ እና ሌሎች ጉዳዮች እንዲሁም አስቸኳይ ውይይት እና ድርድር እንዲጀመር፣ ለታጣቂዎች ግልጽ ጥሪ እንዲደረግ እና የፖለቲካ እሥረኞች እንዲፈቱ የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበው ነበር ብለዋል።


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ጋር ትወያዩ 
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ጋር ትወያዩ ምስል Office of the Prime Minister/Reuters

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ጋር ትወያዩ

This browser does not support the audio element.

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ጋር ትወያዩ 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር ዛሬ ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም በጽሕፈት ቤታቸው ተወያዩ። በውይይቱ የተሳተፉ አንድ ፖለቲከኛ የሰላም፣ የፀጥታ፣ የሕገ መንግሥት፣ የኢኮኖሚ እና ሌሎች ጉዳዮች እንዲሁም አስቸኳይ ውይይት እና ድርድር እንዲጀመር፣ ለታጣቂዎች ግልጽ ጥሪ እንዲደረግ እና የፖለቲካ እሥረኞች እንዲፈቱ የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበው ነበር ብለዋል። 

ለውይይቱ ተጋብዘው ካልተሳተፉ የፓርቲ መሪዎች መካከል አንደኛው ደግሞ "ሀገሪቱ ካለችበት ሁኔታ ጋር ተመጣጣኝ እና በቂ ውይይት የሚካሄድበት ስላልሆነ ጊዜ ማጥፋት እንዳይሆን ብለን" ከመሳተፍ ተቆጥበናል ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ደግሞ "ሁሉን አቀፍ ጠቀሜታ ባላቸው" ባሏቸው ሀገራዊ ጉዳዮች "መግባባት መፍጠርን የተመለከተ ውይይት" ስለማድረጋቸው በማሕበራዊ መገናኛ ዐውታሮች ጽፈዋል። 

በዛሬው ውይይት ምን ምን ጉዳዮች ተነሱ ?

የፓርቲ መሪዎች ከክልል ርእሠ መስተዳድሮች እና ከዋና ዋና ከተሞች ከንቲባዎች ጋር ከዚህ በፊት ውይይቶች መደረጋቸውን እና ይህም የሚነሱ ጥያቄዎች በየደረጃው ባሉ ባለ ሥልጣናት ምላሽ እንዲሰጥባቸው ለመድረግ መሆኑን፣ ትናንት ደግሞ ሱሉልታ ከተመ በሚገኘው የአፍሪካ አመራር አካዳሚ ከገዢው ብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ጋር የፓርቲዎች ኃላፊዎች በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መነጋገራቸውን ተሳታፊዎች ገልፀዋል። 

ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በነበረው ውይይት የተሳተፉ ፖለቲከኛ የሰላም፣ የፀጥታ፣ የሕገ መንግሥት፣ የኢኮኖሚ እና ሌሎች ጉዳዮች እንዲሁም አስቸኳይ ውይይት እና ድርድር እንዲጀመር የሚሉ ሀሳቦች፣ ለታጣቂዎች ግልጽ ጥሪ እንዲደረግና የፖለቲካ እሥረኞች እንዲፈቱ የሚሉ ጥያቄዎችም ቀርበው እንደነበር ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል። ከዚህም ባለፈም የፖለቲካ ምህዳሩን የሚያጠቡ የተባሉ  እንቅስቃሴዎች እንዲቆሙ ሀሳቦች ተነስተዋል ብለዋል። 

"ሰፋፊ የማንነት እና በክልል ደረጃ እንደራጅ" የሚሉ የመዋቅር ጥያቄዎች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ መቅረባቸውን የኢሕአፓ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት መጋቢ ብሉይ አብርሃም ሃይማኖት ገልፀዋል። ኢትዮጵያ "ኢኮኖሚዋ ደቋል፣ የሰላምና ፀጥታ ጉዳይ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል፣ ሕዝቧ ተሰቃይቷል፣ ወጣቱ ተስፋ ቆርጧል፣ ይህ ሁሉ መፍትሔ ያሻዋል" ግን ውይይቱን እንደጠበቅነው አላገኘነውም ሲሉም ምላሽ ሰጥተዋል። 

ጥሪ ደርሷቸው በውይይቱ ያልተሳተፉት ምን ይላሉ ?

ለውይይቱ የቀረበው ጥሪለሁሉም ፓርቲዎች ስለመቅረቡ ሰምተናል። "አካሄዱ ላይ አለባብሶ ለማለፍ ስለሚሞከር፣ ሀገሪቱ ካለችበት ሁኔታ ጋር ተመጣጣኝ እና በቂ ውይይት የሚካሄድበት ስላልሆነ ጊዜ ማጥፋት እንዳይሆን ብለን" መሳተፍ አልፈለግንም ሲሉ በውይይቱ ያልተሳተፉት የኦፌኮ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ሀሳባቸውን አጋርተውናል። "ማሰሪያ የሌላቸው" ያሏቸው ውይይቶች በተደጋጋሚ መደረጋቸውን የሚጠቅሱት ፖለቲከኛው፣ እነዚህ ውይይቶች ኢትዮጵያን ከአጠቃላይ ቀውስ ሊያወጡ አልቻሉም ባይም ናቸው። 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ጋር ትወያዩ ምስል Office of Prime minister of Ethiopia

ይህ ከሆነ መፍትሔው ምንድን ነው ትላላችሁ? ያልናቸው  ፕሮፌሰር መረራ አንድም ድርድር፣ ሁለትም ማሰሪያ ያላቸው ውይይቶችን መድረግ ብለዋል። ይህን መፍትሔ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እየሠራው ነው ይባላል ብለን ለጠየቅናቸውም በተቋሙ ላይ የገለልተኝነት እና የታማኝነት ጥያቄ በመንሳት ውድቅ ያደርጉታል። ውይይት በተደጋጋሚ ይደረጋል የሚሉት ፕሮፌሰር መረራ ይህ ከሆነ ሰላምና መረጋጋት ማየት ሲገባን በተቃራኒው "ሀገሪቷ በታሪኳ ያላየችው አጠቃላይ ቀውስ ውስጥ ስትገባ ታያለህ" በማለት እውነተኛ ያሉት ውይይት እንዲደረግ ጠይቀዋል። 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምን አሉ? 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሦስት ወራት በፊት ከፓርቲ መሪዎች ጋር "በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገን ነበር" በማለት፤ የዛሬው ውይይት የዚያ ተቀጥላ መሆኑን ተናግረዋል። "ሁሉን አቀፍ ጠቀሜታ ባላቸው" ባሏቸው ሀገራዊ ጉዳዮች "መግባባት መፍጠርን የተመለከተ" ውይይት ስለማድረጋቸውም ጽፈዋል። በውይይቱ አብዛኞቹ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፈዋል ተብሏል።  ኮከስ የተባለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ ግን ዛሬም እንዳልተሳተፈ ለማወቅ ችለናል።

 

ሰለሞን ሙጬ 

አዜብ ታደሰ 

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW