1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጣሊያን ሴት ጠይቅላይ ሚኒስትር መረጠች

ሰኞ፣ መስከረም 16 2015

ትናንት ጣሊያን ውስጥ በተደረገው ምርጫ በጆርጂያ ሜሎኒ የሚመራው የሀገሪቱ ቀኝ ፓርቲዎች ጥምረት አሸናፊ ሆኗል።ጥምር ፓርቲያቸው ያሸነፈው ሜሎኒ አስተዳደራቸው ሁሉንም የጣሊያን ዜጎች በእኩል ያገለግላል ብለዋል። እንዲያም ሆኖ ሜሎኒ የሀገር አመራር ልምድ የላቸውም እየተባለ ነው።

Wahl in Italien | Wahlabend in der FdI Parteizentrale
ምስል Gregorio Borgia/AP/picture alliance

የጣሊያን ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር

This browser does not support the audio element.

ትናንት በተካሄደው ምርጫ  ዋናው የጥምረቱ አባል የወይዘሮ ሜሎኒ ፓርቲ የሆነው የጣሊያን ወንድሞች ፓርቲ 26 ከመቶ በማግኘት ትልቁ ፓርቲ ሲሆን ከሌሎቹ ተጣማሪዎቹ ማለት በስደተኞች ላይ ጠንካራ አቋም ያራምዳሉ በሚባሉት ማቲዎ ሳልቪኒ የሚመራው የሊግ ፓርቲና በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስተር ሲልቪዮ ቤርሉስኮኒ ሚመራው ፎርሳ ኢጣሊያ ፓርቲ  ጋር 44 ከመቶ ድምጽ በማግኘነት መንግሥት ለመመስረት የሚያስችል የፓርላማ መቀመጫ ማሸነፋቸው ተገልጿል። ወይዘሮ ሜሎኒ ፓርቲያቸውና ጥምረቱ በአጠቃላይ ማሸነፉ እንደተሰማ ሌሊት ላይ ለደገፊዎቻቸው ባሰሙት ንግግር « ይህችን አገር እንድንመራ ከተመረጥን ሁሉንም ጣሊያናውያን ነው በእኩልነት የምንምራው። ዜጎችን የሚከፋፍሉትን ሳይሆን አንድ የሚያደረጉትን ፕሮግራሞች ነው የምናራምደው» በማለት መንግሥታቸው ታማኝነቱ ለመረጧቸው ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ጣሊያኖች እንደሚሆን ቃል ገብተዋል።  

የ45 ዕድሜ ዓመቷ ወይዘሮ ሜሎኒ  በመንግሥት አመራርነት ልምድ እንደሌላቸው የሚነገር ሲሆን፤  የአጋር ፓርቲዎቹ መሪዎች ልምድ ለመንግሥታቸውና አመራራቸው ተጨምሪ እሴት ሊሆን እንደሚችል ይጠበቃል። ያም ሆኖ ግን የወይዘሮ ሚሊኖ መንግሥት በጣሊያን ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ ወደ ሥልጣን የመጣ የመጀመሪያው የቀኝ ፓርቲና መንግሥት  እንደሆነ ነው የሚነገረው።  

ጆርጂያ ሜሎኒምስል Andreas Solaro/AFP/Getty Images

የወይዘሮ ሜሎኒ ፓርቲ ከሦስት አመት በፊት በተደረገ ምርጫ 4 ከመቶ ብቻ ድምጽ በማግኘቱ በጣሊያን ፖለቲካ የነበረው ተጽኖ አነስተኛ የነበር ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት ግን  ትልቁ ፓርቲ በመሆን ለማሸነፍ መብቃቱና መሪዋ የጣሊያን የመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስተር ለመሆን መብቃታቸው በጣሊያን ፖለቲካ የተፈጠረውን የአስተሳሰብ ለውጥ የሚያሳይ ነው እየተባለ ነው።  

ጣሊያን በአውሮፓ ሕብረት ሦስተኛ ትልቁ ኢኮኖሚ ስትሆን፤ የስሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት ኔቶ አባልም በመሆኗ በሕብረቱ ዘንድ ትልቅ ተጽዕኖ ፈጣሪ አገር ናት።፡ የአውሮፓ ሕብረት በአሁኑ ወቅት በዩክሬን ጦርነትና በሩሲያ ላይ እየወሰደ ባለው እርምጃ ምክኒያት ለከፍተኛ የሀይል አቅርቦትና  ለኑሮ ውድነት ችግር የተጋለጠ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፤ ችግሩን ለመቋቁም የአባል አገራቱን አንድነትና ትብብር አጥብቆ ይፈልገዋል። ከዚህ አንጻር የወይዘሮ ሜሎኒ ጥምር ፓርቲ በጣሊያን ወደ ሥልጣን መምጣቱ  በተለይ ለሕብረቱ ባለሥልጣኖች ምቾት የሚሰጥ እንዳልሆነ ነው የሚነገረው። የጥምረቱ አባል ሊግ ፓርቲ መሪ ማቲዮ ሳልቪኒ በተለይ በፈላሲያንና ስደተኞች ላይ የከረረ አቋም እንዳላቸው የሚታወቅ ሲሆን፤ ሲልቪዮ ቤርሉስኮኒም ፕሬዝዳንት ፑቲንን በጦርነት እንዲገፉ ያድረገው የህብረቱ ፖሊሲ ነው በማለት በሩሲያ ላይ በሚወስዱት የማዕቀብ እርምጃዎች ደስተኛ እንዳልሆኑ ነው የሚነገረው። ሚስተር ዳሪዮ ፋብሪ የተባሉ ዶሚኖ የተሰኘው የጣሊያን የፖለቲክ መጋዚን ዋና አዘጋጅም  የማዕቀብ እርምጃዎች በአጠቃላይ በጣሊያን በበጎ እንደማይታዩና ተመራጩ  መንግሥትም ይህንን የህዝቡን ስሜት ሊያንጸባርቅ ይችላል ነው የሚሉት። ከዚህ በተጨምሪም የሕብረቱ የብራስልስ ሹማምንት በአባል ሃገራት ሉዓላዊነት ላይ ጣልቃ ይገባሉ፤ ከተሰጣቸው ሥልጣን በላይም ውሳኔዎችን ያስተላለፋሉ በማለት ለሚከራከሩት እንደ ሀንጋሪና ፖላንድ የመሳሰሉ አባል መንግሥታት አዲሱ የጣሊያን መንግሥት ተጨማሪ ሀይልና ድምጽ ሊሆናቸው ይችላል እየተባለ ነው። የፖላንድና የሀንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትሮች ቀድመው ለወይዘሮ ሜሎኒ የእንኳን ደስ አለዎት መልክት ማስተላለፍ የሚገልጸውም ይህንኑ ነው ባይ ናቸው ተንታኖች።  ወይዘሮ ሜሎኒ ግን ሕብረቱ በዩክሬን ላይ የወስደውን እቋም እንደሚደግፉና አገራቸውም በኔቶ አባልነቷ እንደምትቀጥል በመግለጽ ጣልያን አሁንም አውሮፓዊት እንደሆነች እንደምትቀጥልና የሚፈጠር አዲስ ነገር እንደማይኖር እያሳሰቡ ነው።  በሌላ በኩል ግን የወይዘሮ ሜሌኖ መንግሥት ምን ያህል ግዜ ሊቆይ ይችላል የሚለው ካሁኑ እያነጋገረ ነው። ታዛቢዎች በጣሊያን አንድ መንግሥት የሚቆየው በአማካይ 20 ወራት እንደሆነ በመግለጽ  የወይዘሮ ሜሎኖ መንግሥትም ምን ያህል ጊዜ ሊቆይ እንደሚችል በትክክል መናገር አይቻልም ነው የሚሉት ። ጣሊያን ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት ወዲህ ያሁኑን አዲስ መንግሥትና ጠቅላይ ሚኒስትሯን ሳይጨምር  67 መንግሥቶችና 30 ጠቅላይ ሚኒስትሮች አይታለች።  

የድምጽ ቆጠራውምስል Michele Nucci/LaPresse/AP/picture alliance

ገበይው ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ታምራት ዲንሳ 

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW