1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ታጣቂዎች የሰገን ከተማን ለቀው ወጡ ፤ በመቶ ሚሊዮኖች ብር የሚቆጠር ውድመት ደረሰ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 16 2016

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮንሶ ዞን የሰገን ዙሪያ ወረዳ የአስተዳደር መቀመጫ የሆነውን የሰገን ከተማን ከባለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ተቆጣጥረው የነበሩ ታጣቂዎች አካባቢውን ለቀው መውጣቸው ተነግሯል ፡፡ ታጣቂዎቹ ትናንት ከተማውን ለቀው የወጡት የመከላከያ ሠራዊት አባላት ወደ ከተማው መግባታቸውን ተከትሎ መሆኑን ነዋሪዎች ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል ፡፡

Äthiopien Stadt Segen Konso
ምስል Basire Balcha /DW

በኮንሶ ሰገን ታጣቂዎች በህይወት እና ንብረት ላይ ብርቱ ጉዳት አድርሰዋል

This browser does not support the audio element.


የሰገን ከተማ ከታጣቂዎቹ መውጣት በኋላ  
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮንሶ  ዞን የሰገን ዙሪያ ወረዳ የአስተዳደር መቀመጫ የሆነውን የሰገን ከተማን ከባለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ተቆጣጥረው የነበሩ ታጣቂዎች አካባቢውን ለቀው መውጣቸው ተነግሯል ፡፡ ታጣቂዎቹ ትናንት ከተማውን ለቀው የወጡት የመከላከያ ሠራዊት አባላት ወደ ከተማው መግባቱን ተከትሎ መሆኑን አንድ የከተማው ነዋሪ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል  ፡፡
ከቀናት ቆይታ በኋላ ትናንት የመከላከያ ሠራዊት ወደ ከተማው ሲገባ መመልከታቸውን የጠቀሱት ነዋሪው “ በከተማው ሠራዊቱ ሲገባ ታጣቂዎቹ አስቀድመው አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል ፡፡ አሁን ሠራዊቱ በአካባቢው እየተንቀሳቀሰ በመሆኑ አንጻራዊ መረጋጋት እየመጣ ነው  ፡፡ በድንጋጤ ከከተማው የሸሹና የተደበቁ ነዋሪዎችም እየወጡ ነው ፡፡ ይህ ምን ያህል ዘላቂ ይሆናል የሚል ሥጋት አለብን  “ ብለዋል ፡፡

የታጠቁ ኃይሎች የሰገን ከተማን መቆጣጠራቸውን የከተማው ነዋሪዎች ገለፁ
የወደሙት የመንግሥት መሥሪያቤቶች
ታጣቂ ሀይሉ በኮንሶ ዞን የሰገን ዙሪያ ወረዳ መዋቅርን በኃይል ለመናድ ሞክሮ አልተሳካለትም ያለው የኮንሶ ዞን መስተዳድር በበኩሉ በ8 ፖሊስ አባላትና 5 ሲቪል ነዋሪዎች ላይ የግድያ ተግባር መፈጸሙን አስታውቋል፡፡ በተጨማሪም በ23 የመንግሥት መሥሪያቤቶች ላይ ሠፊ የንብረት ዝርፊያና ውድመት በመፈጸም ከ600 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት ማድረሱን የዞኑ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ሃላፊ አቶ ሠራዊት ዲባባ ዶቼ ቬለ ገልጸዋል  ፡፡

ታጣቂ ሀይሉ በኮንሶ ዞን የሰገን ዙሪያ ወረዳ መዋቅርን በኃይል ለመናድ ሞክሮ አልተሳካለትም ያለው የኮንሶ ዞን መስተዳድር በበኩሉ በ8 ፖሊስ አባላትና 5 ሲቪል ነዋሪዎች ላይ የግድያ ተግባር መፈጸሙን አስታውቋል፡፡ምስል Konso zone government Communication office

ኮንሶ፣የድርቅ መዘዝ
ከመሆኑ በፊት
የሰገን ዙሪያ ወረዳ የታጣቂዎች እንቅስቃሴ የሚስተዋልበት መሆኑን የጠቀሱት አንድ የአካባቢው ተወላጅ “ የዞኑም ሆነ የክልሉ አስተዳደር የከተማውን ህዝብ ደህንነት ለመጠበቅ ትኩረት አልሰጠም “ በማለት  ወቅሰዋል ፡፡ ጥቃቱ ከመድረሱ በፊት ጥንቃቄ ማድረግ ይቻል ነበር ያሉን ሥማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ሌላው የሰገን ከተማ ነዋሪ “ የሽብር ቡድኑ ከተማውን ተቆጣጥሮ የሚፈልገውን ሲገድል ፤ የመንግስት መሥሪያቤቶችን ሲዘርፍና ሲያቃጥል ነበር ፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘውና አዲስ ገበሬ በተባለው ቦታ የፀጥታ ሠራዊት አባላት ነበሩ ፡፡ ለመከላከልም ሆነ ተጨማሪ ሀይል እንዲመጣላቸው ጥረት ሲያደርጉ አላየንም ፡፡ የድርጊቱ ፈጻሚዎች አሁንም ነገ ተመልሰው ሥለመምጣታቸው ዋስትና የለንም “ ብለዋል ፡፡

የሰገን ዙሪያ ወረዳ የታጣቂዎች እንቅስቃሴ የሚስተዋልበት መሆኑን የጠቀሱት አንድ የአካባቢው ተወላጅ “ የዞኑም ሆነ የክልሉ አስተዳደር የከተማውን ህዝብ ደህንነት ለመጠበቅ ትኩረት አልሰጠም “ በማለት  ወቅሰዋል ፡፡ምስል Konso zone government Communication office

መፍትሄ ያጡት የኮንሶና አካባቢው ተፈናቃዮች
አካባቢው የፀጥታ ችግር እንዳለበት እየታወቀ ትኩረት አልተሰጠውም በሚለው ቅሬታ ላይ ዶቼ ቬለ የኮንሶ ዞን የመንግሥት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ሃላፊ አቶ ሠራዊት ዲባባን ጠይቋል ፡፡ ጥቃቱ በወረዳው እንዴት ሊከሰት እንደቻለና በታጣቂው ላይ እየተወሰደ በሚገኘው እርምጃ ላይ በቀጣይ በጸጥታ ሃላፊዎች ዝርዝር ማብራሪያ የሚሰጥ ይሆናል የሚል ምላሽ ሰጥተዋል ፡፡
ሸዋንግዛው ወጋየሁ

ታምራት ዲንሳ

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW