1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ጤናና አካባቢ፤ የአካባቢ በካዮችን ወደ ፍርድ ማቅረብ

ማክሰኞ፣ መስከረም 27 2018

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ለረዥም ዓመታት በየዕለቱ በሚያወጣቸው የእርድ ተረፈ ምርቶች የአካባቢ ብክለት እየፈጸመ እንደሆነ የአካባቢው ነዋሪዎችና እግር ጥሏቸው በአካባቢው በተሽከርካሪም ሆነ በእግር የሚጓዙ የከተማዋ ነዋሪዎች ያማርራሉ።

«ቁም ለአካባቢ» የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ አገር በቀል ድርጅት መስራችና ዋና ዳይሬክተር አቶ መልካሙ ኦጎ ከአውደ ጥናት ተካፋዮች ጋር
«ቁም ለአካባቢ» የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ አገር በቀል ድርጅት መስራችና ዋና ዳይሬክተር አቶ መልካሙ ኦጎ ከአውደ ጥናት ተካፋዮች ጋርምስል፦ Private

የሕዝብን ጥቅም ለማስከበር ከአካባቢ ጥበቃ ጋር በተያያዘ ስለሚደረግ የፍትህ ሂደት

This browser does not support the audio element.

በተለያዩ የሐገሪቱ አካባቢዎች የአየር፣ የውሃ፣ የድምጽ በአጠቃላይ የአካባቢ ብክለቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ መምጣታቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ። የፋብሪካዎች መስፋፋት፣ የግጦሽና የእርሻ መሬት ፍለጋ፣ የተሽከርካሪዎች መብዛት ለብከለቱ መጨመር ከሚጠቀሱ ዋናዎቹ ናቸው። ለምሳሌ ለአዲስ አበባ ከተማ የአየር ብክለት ተሽከርካሪዎች 28 %፣ ባዮማስ ነዳጅ 18.3 %፣  የአፈር አቧራ 17. 4 % አስተዋፅኦ እንደሚያደርጉ የከተማዋ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በግንቦት ወር 2016 ይፋ ያደረገው መረጃ ያመላክታል። 
የአዲስ አበባ የበካይ ጋዝ ልቀት ኦዲት  የሚለው ጥናት እንዳመላከተው ደግሞ በከተማዋ ከሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች በየዕለቱ 4.8 ሚልዮን ቶን የተቃጠለ በካይ አየር ወይም ካርቦን ይለቃሉ። 44 በመቶ የሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎችም፤ ነጭ ጋዝና ከሰልን ለቤት ውስጥ የምግብ ማብሰያነት ስለሚጠቀሙ በየቀኑ  1.3 ሚልዮን ቶን ካርቦንዳይኦክሳይድ ወደ አካባቢ በመልቀቅ በብክለቱ ላይ የራሳቸውን አስተዋጽኦ ያደርጋሉ። 
በሐገሪቱ የሚፈጸሙ የአየር ብክለት ችግሮችን ለመከላከልና አጥፊዎች ላይ ደግሞ የፍታብሔር ተጠያቂነትን ለማስፈን ዋና ዓላማው አድርጎ የሚንቀሳቀሰው «ቁም ለአካባቢ» የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ አገር በቀል ድርጅት መስራችና ዋና ዳይሬክተር አቶ መልካሙ ኦጎ ድርጅታቸው በአካባቢ ጥበቃ ላይ እያከናወናቸው ካሉ ዋናዋና ተግባራት ኣእዲህ አወጉን።

«የአካባቢ ጥበቃን በተመለከተ የውትወታ ሥራ እንሰራለን። ለመንግስታዊም ሆነ በግል በአካባቢ ጥበቃ ለተሰማሩ ባለሙያዎች ስልጠና እንሰጣለን አካባቢ ጥበቃን የተመለከተሁሉን አቀፍ ስልጠናዎችን እንሰጣለን። ለአካባቢ ማሕበረሰቦች ደግሞ የአካባቢ ጥበቃን በተመለከተ የግንዛቤ ማሳደጊያ ሥራዎች እንሰራለን። ከዚህም ባሻገር አሁን በኢትዮጵያ ውስጥ በልዩነት የምንታወቅበት ለሕዝብ ጉዳዮች ተብሎ አካባቢያዊ ብክለትን ፈጽመዋል ያልናቸው ተቋማትን ፍርድቤት የማቅረብ እየሰራን እንገናለን።»


የሸካ ደን ጭፍጨፋ እንደምሳሌ


የአዲስ አበባ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የ2017 ዓ.ም የ6 ወራት የሥራ  የአፈጻጸም ሪፖርት እንደሚያመላክተው በዚያው ዓመት በአካባቢ ብክለት አድርሰዋል የተባሉ ከ1,700 በላይ አምራችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ከማስጠንቀቂያ እስከ ድርጅት ማሸግ እርምጃ መውሰዱን ያመላክታል። ይሁንና የአካባቢ ብክለት ትርጉም ባለው መልኩ አለመቀነሱን የአካባቢ ጥበቃ ተከራካሪዎች ይገልጻሉ።
ከመዋዕለ ንዋይ ፍሰት፣ የሕዝብ ቁጥር መብዛት፣ ይህን ተከትሎ የእርሻ እና የግጦሽ መሬት ማስፋፋት ጋር ተያይዞ የደኖች መጨፍጨፍ እየተስፋፋ መሆኑን ያወሱት አቶ መልካሙ በሸካ ዞን ባለው ጫካ እየደረሰ ያለው የደን ጭፍቸፋና ያስከተለው የአካባቢ አየር ለውጥ እንዲሆም በሕብረተሰቡ ላይ ያስከተለውን የጤና ችግር እንደምሳሌ አድርገው አንስተዋል። 
« ለምሳሌ የሸካን ደን ማንሳት እንችላለን። የሸካ ደን ለከፍተኛ አደጋ ተጋላጭ ከሆኑ ደኖች አንዱ ነው።  በአካባቢው የኢንቨስትመንት መስፋፋት» ለጣውላ ምርት ለእርሻ ሥራዎች በሚል የደንጭፍጨፋ ስለሚካሄድበት ከፍተና አደጋ ከተጋረጠባቸው ደኖች አንዱ ነው። የዚህ ውጤትም በአይን የሚዳሰስ የአካባቢ ብክለት ውጤት እየታየ ነው። ይህን ተከትሎ እንደ ወባ ያሉ በሽታዎችም እየተስፋፋ ይገናል።»

በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ላይ የተመሰረተ ክስ  

  
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ለረዥም ዓመታት በየዕለቱ በሚያወጣቸው የእርድ ተረፈ ምርቶች የአካባቢ ብክለት እየፈጸመ እንደሆነ የአካባቢው ነዋሪዎችና እግር ጥሏቸው በአካባቢው በተሽከርካሪም ሆነ በእግር የሚጓዙ የከተማዋ ነዋሪዎች ያማርራሉ። ድርጅቱበካይ ጋዞችን በማውጣት እየፈጸመ ያለውን የአካባቢ ብክለት እንዲያሻሽል በሕብረተሰቡና በሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በየጌዜው የሚሰጡትን ማስጠንቀቂያዎች ተግባራዊ ባለማድረጉ በቁም ለአካባቢ ድርጅት ክስ ተመስርቶበታል። የክሱ ይዘት
«በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ የፍትሐብሔር ምድብ ችሎት የቀረበው ክስ፤ የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት በመኖሪያ ቤቶች አካባቢ ሆኖ አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ ማንም ሰው አካባቢን ሊበክል ወይም በሌላ ሰው በኩል እንዲበከል ማድረግን የሚከለክል አዋጅ ቁጥር 300/95 አንቀፅ 3 ላይ የተቀመጠውን የሕጉ ክፍልን በመተላለፍ  በሚያወጣቸው የእርድ ተረፈ ምርቶች የአካባቢ ብክለት ፈፅሟል የሚል ነው። 
ድርጅቱ የእንስሳት ዕርድና የሥጋ አቅርቦት የሚሰራበት ቦታ በሺዎች የሚቆጠሩ የከተማዋ ነዋሪዎች በትራንስፖርትና በእግር የሚተላለፉበት በታ ላይ ይገኛል። ድርጅቱ በየቀኑ የሚያከማቻቸው የዕርድ ተረፈ ምርቶች ማለትም አጥንት፣ደምና ሌሎች ተረፈ ምርቶች በአግባቡና ደረጃውን በጠበቀ የቆሻሻ አወጋገድ መንገድን ተከትሎ እንደማያስወግድ በክሱ ተብራርቷል።» በማለት ያብራራሉ።

አቶ መልካሙ ኦጎ«ቁም ለአካባቢ» የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ አገር በቀል ድርጅት መስራችና ዋና ዳይሬክተር ምስል፦ Private


ተረፈ ምርቶቹን መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል በሚያስችልቴክኖሎጂ በመታገዝ የሕብረተሰቡን ጤናና አካባቢን በማይጎዳ አገልግሎት ባለማዋሉ፤ ፈሳሾችን ወደ አካባቢው በመልቀቅና ጠጣር ተረፈ ምርቶችን በግቢው በማከማቸት በካይ ጋዞችን በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ላለፉት 30 ዓመታት እየለቀቀና እየበከለ በመሆኑ ፤ ድርጅቱ ይህን ተግባሩን እንዲያቆም በአካባቢው ነዋሪዎች በተደጋጋሚ ቢጠየቅም ተግባራዊ ባለማድረጉ አካባቢን በመበከል የሕብረተሰቡን ጤናን የሚጎዳ ተግባር መፈጸሙን የክስ መዝገቡ ይዘረዝራል። 
በመሆኑም የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ካለበት ቦታ እንዲነሳና በአጠቃላይ በሕብረተሰቡ ላደረሰው የጤና፣ የኢኮኖሚና የሞራል ጉዳት በተመለከተ ወደፊት በባለሙያ ተጠንቶ የፍሐብሔር ክስ ማቅረብ እንዲቻል ውሳኔ እንዲሰጥ ነው የአካባቢ ተሟጋች ድርጅቱ ዳኝነት መጠየቁንና በፍርድ ቤት ተወስኖ የአፈጻጸም ፋይል መከፈቱን አቶ መልካሙ አስረድቷል።

የሀዋሳ ደረቅ ቆሻሻ መጣያ

ሌላው ከአካባቢ ብክለት አንጻር የክስ ክርክር ፋይል ከከፈተባቸው የሐዋሳ ከተማ ማዘጋጃቤት ነው። በከተማዋ ዲያስፖራ ሰፈር አልያም ቆሼ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የከተማዋ ጠቅላላ ደረቅ ቆሻሻ የሚጣለው በዚያ አካባቢ ነው። በአካባቢው የሚኖሩና ወደ አካባቢው የሚንቀሳቀሱ የከተማዋ ነዋሪዎች ከሚያጋጥናቸው አፍንጫ በጥስ መጥፎ ሽታ በተጨማሪ በተፈጠረው የአየር ብክለት በሕብረተሰቡ ጤና ጉዳት እያደረሰ መሆኑን የአካባቢው ብክለት በማድረስ እንዲከሰስ ማድረጋቸውን ባለሙያው ያክላሉ። ጉዳዩን የተመለከተው ፍርድቤትም ከቦታው እንዲነሳ ውሳኔ መስጠቱን በማከል።


«ተመዘገቡ» ስለተባሉ ውጤቶች


ቁም ለአካባቢ የሕብረተሰቡን ጥቅምን መሰረት በማድረግ አካባቢን በክሏል ባላቸው ድርጅቶች ላይ በሚመሰርታቸው የፍርድቤት ክርክሮች፣ የአካባቢ ብክለት ቁጥጥር፣ የተፈጥሮ ሐብት እንክብካቤ፣ የአካባቢ ደህንነትና ጤና እንዲሁም ሌሎች ተዛማጅ ስራዎች በርካታ ውጤቶች  ማስመዝገብ መጀመራቸውን አቶ መልካሙ ይገልጻሉ።

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
ፀሐይ ጫኔ


 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW