ጤናና አካባቢያችን በ2002ዓ,ም
ማክሰኞ፣ ጳጉሜን 2 2002ማስታወቂያ
በአሮጌዉ ዓመት የተጀመሩ አበረታች ተግባራት በመጪዉ ዓመት ይበልጥ ተስፋፍተዉ ዉጤት ለማየት ግን ጅምሩን አጠናክሮ ማስፋፋት ይጠይቃል። በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የጤና አገልግሎትን ለማስፋፋት የተቀየሰዉ ስልት፤ የወባ በሽታን ለመቆጣጠር እንዳስቻለ ሁሉ፤ የእናቶችና ህፃናትን ሞት ይበልጥ በመቀነስ፤ የHIV AIDS ንም ስርጭት በመግታት፤ የተመድ ካለመዉ የልማት ግብ ለመድረስ መጣር ግድ ይሆናል። የተራቆቱ አካባቢዎችን ከሰዉና እንስሳት ንክኪ በማግለል ለማልማት የተጀመረዉ ጥረት፤ በጎነቱ ባያነጋግርም፤ የነበሩ የአገሪቱን ዉሱን የደን ሃብቶችምi በየደረጃዉ አላግባብ ከሚወድሙበት አካሄድ ማዳን ያስፈልጋል።
ሸዋዬ ለገሠ
ተክሌ የኋላ