1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጥሪ የተደረገላቸው የቀድሞ የመከላከያ ሠራዊት 

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 30 2014

የሀገር  መከላከያ  ሠራዊት  ሀገርን ለመጠበቅ  እገዛ  እንዲያደርግ ያቀረበውን ጥሪ  መንግሥት መቀበሉ አንዳስደሰተው የኢትዮጵያ የቀድሞ ሠራዊት አባላትን ያሰባሰበው ማኅበር ገለጸ። ለመንግሥት ያቀረብነው ጥያቄ ተመልሷል ያለው የቀድሞ ሠራዊት የድጋፍና የልማት ማኅበር፤ ኢትዮጵያ አሁን የምትገኝበት ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ መሆኑ አመልክቷል።

Äthiopien Berhanu Amare
ምስል Solomon Muchie/DW

«ሠራዊቱ ደስተኛ ነው»

This browser does not support the audio element.

የሀገር  መከላከያ  ሠራዊት  ሀገርን ለመጠበቅ  እገዛ  እንዲያደርግ ያቀረበውን ጥሪ   መንግሥት መቀበሉ አንዳስደሰተው የኢትዮጵያ የቀድሞ ሠራዊት አባላትን ያሰባሰበው ማኅበር ገለጸ። ሀገርን ማስከበር፣ ሠራዊትን ማስተማር፣ ማሰልጠን እና ማገልገል የሚያስችል ብቃት እያለው እጅን አጣጥፎ መቀመጡ ተገቢ እንዳልሆነ በማመን፣ ለመንግሥት ያቀረብነው ጥያቄ ተመልሷል ያለው የቀድሞ ሠራዊት የድጋፍና የልማት ማኅበር፤ ኢትዮጵያ አሁን የምትገኝበት ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ መሆኑ አመልክቷል። የቀድሞው ሠራዊት በኢትዮጵያ አንድነትና ሉዓላዊነት የማይደራደር መሆኑን የጠቀሱት የማኅበሩ ፕሬዝደንት የሃምሳ አለቃ ብርሃኑ አማረ፤ ሠራዊቱ ከውጊያ ባሻገር ልዩ ልዩ ተቋማትን በመጠበቅ ኃላፊነት የሚሠማሩ ወጣት የፀጥታ አካላት ወደ ግንባር እንዲሄዱ ለተቋማቱ ጥበቃ ሽፋን በመስጠትም ለማገልገል ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።  

ሰለሞን ሙጬ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW