ጥቃት በኦታዋ ካናዳ ምክር ቤት
ሐሙስ፣ ጥቅምት 13 2007ማስታወቂያ
የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ስቴፈን ሀርፐር ለምክር ቤት ባደረጉት ንግግር የሀገሪቱ የደህንነትና ፀጥታ ተቋማት የማሰርና የመፈተሽ ስልጣን እንዲሰጣቸዉ ታቅዷል። ትናንት በኦታዋ ምክር ቤት አቅራቢያ አንድ ወታደር ገድሎ ወደምክር ቤት የዘለቀዉ የ32ዓመት ጎልማሳ ምክር ቤቱ ዉስጥና በአቅራቢያዉ በሚገኝ የገበያ አዳራሽ ያርከፈከፋቸዉ ጥይቶች ብዛት አጃቢ ያለዉ አስመስሎ ፖሊሶችን ቢያደናግርም ዛሬ የወጡ ዘገባዎች እንደሚሉት ብቻዉን ነበር። የርሱም ህይወት አልፏል። ጥርጣሬዉን ማረጋገጥ የሚሻዉ ፖሊስ ግን ክትትሉን እንዳላቆመ ገልጿል። ከሞላ ጎደል በተረጋጋ ፀጥታዋ በምትታወቀዉ ካናዳ የደረሰዉ ጥቃት ዜጎችን ብቻ ሳይሆን መንግሥትንም ያደናገጠ ብሎም ያባነነ መሆኑ እየተገለጸ ነዉ። ስለሁኔታዉ የዋሽንግተን ዲሲ ዘጋቢያችን አበበ ፈለቀን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
አበበ ፈለቀ
ሸዋዬ ለገሠ
አርያም ተክሌ