1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«ጦርነት በጎዳቸው በአፋር በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች የሚጣሉ ጨቅላ ሕፃናት ቁጥር ጨምሯል»

ሰኞ፣ ጥቅምት 18 2017

"በግጭት ዐዉድ ያሉ ሴቶች እና ሕፃናት አሁንም ፆታን መሠረት ላደረጉ ጥቃቶች ተጋላጭ መሆናቸው መቀጠሉ፣ ለሚደርስባቸዉም ጥቃት ተገቢ ምላሽ የሚሰጥ አከል አለመኖሩ" ችግር መሆኑን ተገልጿል።በመሠረታዊ አቅርቦቶች እጥረት ምክንያት እናቶችና ጨቅላ ሕፃናት በወሊድ ወቅት ለከፋ ችግር እየተጋለጡ የሚሞቱም ቁጥርም እየጨመረ መምጣቱ ተመልክቷል።

ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት ከኦሮምያ ክልል ተፈናቅለው ደብረ ብርሀን መጠለያ ውስጥ የነበሩ ሴቶችና ህጻናት
ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት ከኦሮምያ ክልል ተፈናቅለው ደብረ ብርሀን መጠለያ ውስጥ የነበሩ ሴቶችና ህጻናት ምስል North Shewa Zone communication Office

«ጦርነት በጎዳቸው በአፋር በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች የሚጣሉ ጨቅላ ሕፃናት ቁጥር ጨምሯል» ኢሰመኮ

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከሰኔ 2015 እስከ ሰኔ 2016 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍን የሴቶችና ሕፃናት የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ የምርመራ ውጤትን ለሦስተኛ ጊዜ አውጥቷል።ኮሚሽኑ "በግጭት ውስጥ ባሉ እና በትጥቅ ግጭት ውስጥ በቆዩ" ባላቸው የሀገሪቱ አካባቢዎች "በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች እና በታጣቂ ቡድኖች በተለያየ ጊዜ በሚፈጸሙ ጥቃቶች" ሴቶችና ሕፃናት ለሞት፣ ለአካል ጉዳት እና ለጾታ ጥቃቶች ሰለባ ሆነዋል።

በኢሰመኮ የሴቶች፣ የሕፃናት፣ የአካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሐዋሪያ ለዶቼ ቬለ በሰጡት ተጨማሪ ማብራሪያ በማቆያዎች ስፍራዎች የሚኖሩ ሕፃናት ሰብአዊ አያያዝ ለጥቃት ተጋላጭ በሆኑበት አኳዃን እንደሚገኙ፣ ተፈናቃይ ዜጎች እና በትላልቅ እርሻ ቦታዎች የሚሠሩ ሕፃናት የጉልበት ብዝበዛ እንደሚፈፀምባቸው ገልፀዋል።የአማራ ክልል ተፈናቃዮች አቤቱታ

"በግጭት ዐዉድ ውስጥ ያሉ ሴቶች እና ሕፃናት አሁንም ፆታን መሠረት ላደረጉ ጥቃቶች ተጋላጭ መሆናቸው ቀጥሏል። ከዚያ በተጨማሪ ደግሞ ለሚደርስባቸዉም ጥቃት ተገቢ ምላሽ የሚሰጥ አከል አለመኖሩ" ችግር መሆኑን ገልፀዋል።በተመሳሳይ "በቂ መልሶ የማቋቋም ሥራ ባለመከናወኑ" በመሠረታዊ አቅርቦቶች እጥረት ምክንያት እናቶችና ጨቅላ ሕፃናት በወሊድ ወቅት ለከፋ ችግር እየተጋለጡ የሞት ሁኔታቸዉም እየጨመረ መምጣቱ በግኝቱ ተመላክቷል።

ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት ከኦሮምያ ክልል ተፈናቅለው ደብረ ብርሀን የተጠለሉ ሴቶችና ህጻናትምስል North Shewa Zone communication Office

 

"ከግጭት ዐውድ ዉጪ እያገገሙ አሉ በምንላቸውም ቦታዎች ላይ የፀጥታ ሥጋቶች አሉ። የፍትሕ አስተዳደሩን ጨምሮ ሌሎች መሠረተ ልማቶች ወደ ቦታቸው ስላልተመለሱ እና ተገቢዉን ምላሽ የሚሰጡበት አቋም ላይ ስላልሆኑ አሁንም ጥቃቶች ይበረክታሉ"የትግራይ ሴት ተፈናቃዮች

ጦርነት ክፉኛ በጎዳቸው በአፋር እና በአማራ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልሎች የሚጣሉ ጨቅላ ሕፃናት ቁጥር መጨመሩን በምርመራ ውጤቱ ይፋ ያደረገው ብሔራዊው የመብቶች ጥበቃ ተቋም፤ "የሚሰጣቸው ምክረ ሐሳቦች ተግባራዊ አለመደረጋቸው" ሊታረም የሚገባው መሆኑንም 

ኮሚሽነር ርግበ ገብረሐዋሪያ ገልፀዋል።

 

የትግራዩ ጦርነት ሰለባ የነበሩ ተፈናቃይ ሴቶች ምስል EDUARDO SOTERAS/AFP via Getty Images

"የሚፈፀሙ ምክረ ሐሳቦች አሉ። ግን በምንፈልገው ልክ እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ባሉበት ልክ አይደለም ምላሹ እየተሰጠ ያለው። እኛ ውትወታችንን እንቀጥላለን"።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አሁንም ሁነኛ መፍትሔ ሳያገኙ በቀጠሉ አውዳሚ ግጭቶች እና ያንን ተከትሎ "በተፈጠረው የደኅንነት ሥጋት" በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ በሺህዎች የሚቆጠሩ ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸው አሳሳቢ መሆኑን፣ የጥቃት ሰለባዎችም የተሟላና ሁሉን አቀፍ ድጋፍና እንክብካቤ እንደማያገኙ አስታውቋል።

ሰሎሞን ሙጬ

ኂሩት መለሰ

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW