ጦርነት ያወደማቸው የጤና ተቋማት ተስፋ
እሑድ፣ ታኅሣሥ 24 2014
ማስታወቂያ
ጦርነት ያወደማቸው የጤና ተቋማት ተስፋ
ከአንድ ዓመት በላይ በዘለቀው በሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚደረገው ጦርነት በመሰረተ ልማት ዘርፉ ላይ ከፍተኛ ውድመት እያደረሰ ቀጥሏል። እስካሁን በትግራይ ክልል ስለደረሰው የጉዳት መጠን በትክክል የሚታወቅ ነገር ባይኖርም ጦርነቱ በተዛመተባቸው የአፋር እና አማራ ክልሎች መንግሥት እንደገለጸው ከ2000 በላይ የጤና ተቋማት ተዘርፈዋል፤ ወድመዋል፤ ከአገልግሎት ውጭም ሆነዋል። እንደኢትዮጵያ ባለ የጤና ዘርፉ የተዳከመ ሀገር የደረሰው ጉዳት በተገልጋዩ ኅብረተሰብ ላይ የሚያስከትለው ጫና ቀላል እንዳልሆነ ይታመናል። ስለደረሰው ጉዳት እየተወራ ዛሬም ጦርነቱ አለማባራቱ ቀጣይ ሊከተል የሚችለውን ውድመት አሳሳቢ ያደርገዋል። በአማራ እና አፋር ክልል የወደሙ የጤና ተቋማትን መልሶ የማቋቋም እንቅስቃሴ መጀመሩ አንድ ነገር ቢሆንም ከውጭ ምንዛሪ እጥረቱ ጋር ተያይዞ የመድኃኒት እና የህክምና መገልገያዎች አቅርቦትም ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ ነው። የደረሰውን ጉዳት በማንሳት፣ ካለው ላይ የተቀነሱትን የጤና ተቋማት ዳግም ለአካባቢው ማኅበረሰብ አገልግሎት እንዲሰጡ የማድረግ ጥረት እና ያለውን አቅም በሚመለከት የተካሄደውን ውይይት የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ያድምጡ።
ሸዋዬ ለገሠ