ጽጌረዳዉ ሰኞ በኮሎኝ
ሰኞ፣ የካቲት 16 2001ማስታወቂያ
ለበዓሉ የሚደረገዉ ዝግጅት ለገናም ሆነ ፋሲካ ከሚደረገዉ አይተናነስም ማለት ይቻላል፤ ከልብስ ዝግጅቶች አንስቶ መጠጥ ሁሉ በዓይነት በዓይነቱ ተስተካክሎ በየገበያ አዳርሾች በማስታወቂያ ታጅቦ ይቀርባል። ሃይማኖታዊ ዳራ እንዳለዉ የሚናገሩ የእምነት ሰዎችም አሉ። ለዓብይ ፆም እንደመዳረሻ የሚቀርብ በመሆኑም፤ ረቡዕ ዕለት በካቶሊክ ቤተክርስቲያን የዚሁ ቀጣይ ዝግጅት ይኖራል፤ ርኩስ መንፈስን የማቃጠል። የዛሬ ሳምንት ሰኞ ታዲያ ፆም ለጿሚዎቹ ይጀመራል።