ፈረንሳይና ስደተኖች
ሐሙስ፣ ነሐሴ 28 2007ማስታወቂያ
ሰኞ ዕለት ከአዉሮጳ ኅብረት ኮሚሽን ተወካዮች ጋር በመሆን ወደፈረንሳይዋ የወደብ ከተማ ካሌ ያቀኑበት የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ማኑዌል ቫልስ እዚያ የሚገኙ ስደተኞችን ሁኔታ ከተመለከቱ በኋላ 1,500 ስደተኞችን ማስተናገድ የሚችል አዲስ የስደተኞች መቀበያ ማዕከል ካሌ ላይ ሀገራቸዉ እንደምትከፍት አስታዉቀዋል። ስደተኞችም እንደሰዉ ሊከበሩና ሰብዓዊ መብታቸዉ ሊጠበቅ ይገባልም ማለታቸዉ ተሰምቷል። ይሁን እንጂ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲሱ ዕቅድ በሌሎቹ የፈረንሳይ ፖለቲከኞች እና ሰብዓዊ ርዳታ ሰጪ ተቋማት ተተችቷል። ወደእንግሊዝ ለመሻገር የሚመኙ ስደተኞች ወደሚከማቹባት የወደብ ከተማ ካሌ ደርሳ የተመለሰችዉ የፓሪሷ ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ ዝርዝሩን ልካልናለች።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ