1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፈተና ያቀጨጨው የኢትዮጵያ ፕረስ

እሑድ፣ ሐምሌ 16 2015

"ጋዜጠኞች ስራቸውን በአግባቡ እንዳያከናውኑ ሆን ተብሎ ለመሆናቸው በቂ ጥርጣሬ ሊያሳድር በሚችል መልኩ ቢሮአቸው እየተሰበረ የስራ እቃዎቻቸውን እንዲዘረፉም እየተደረገ ነው።"

Illustration | Mikrofon in Ketten
ምስል Sorapop/Panthermedia/imago images

ፈተና ያቀጨጨው የኢትዮጵያ ፕረስ

This browser does not support the audio element.

     
በኢትዮጵያ እንደ የመንግስታቱ መቀያየር የመገናኛ ብዙሃን ላይ የሚደርሰው ጫናም አንዴ ከፍ አንዴ ዝቅ ሲል ይስተዋላል። በድምር ውጤቱ ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ መምጣቱን ግልጽ እየሆነ ነው። በፕረሱ ጉዳይ ከሚስተዋሉ ችግሮች አንደኛው የሕግ እና የአሰራር ችግሮች ሲሆኑ ሁለተኛው ደግሞ በአስፈጻሚው አካል የሚደርሱ አፈና፣ እስር እና ዘርፈብዙ ማስተጓጎሎች ተብለው በጥቅሉ ሊጠቀሱ ይችላሉ፤ ተግዳሮቶቹም የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ሥራቸውን በአግባቡ እንዳያከናውኑ፤ ሕዝቡም ከነዚህ ማግኘት የሚገባውን ጥቅሞች እንዳያገኝ ዕንቅፋት እየፈጠሩ እንደሆነ ብዙዎች በምሬት ይገልጻሉ።
አሁን አሁን ደግሞ ጋዜጠኞች ስራቸውን በአግባቡ እንዳያከናውኑ ሆን ተብሎ ለመሆናቸው በቂ ጥርጣሬ ሊያሳድሩ በሚችል መልኩ ቢሮአቸው እየተሰበረ የስራ እቃዎቻቸውን እንዲዘረፉም እየተደረገ ነው። በፕረሱ የስራ ሂደት እያጋጠሙ ያሉ የሕግና የአፈጻጸም ተግዳሮቶችና ይሆናሉ የሚባሉ የመፍትሄ ሐሳቦች ላይ የተካሄደውን ውይይት ለማዳመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW