1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

እኛ ኢትዩጵያውያን በአዲስ አመት ስናከብር ለየት ያለ ባህልና ስርአቶችን አሉን

ቅዳሜ፣ ጳጉሜን 5 2014

እኛ ኢትዩጵያውያን በአዲስ አመት ስናከብር ለየት ያለ ባህልና ስርአቶችን አሉን ከነዚ ውስጥ አንዱ ጠዋት ተነስቶ በቀዝቃዛ ውሀ ገላን መታጠብ ከዛ መልስ በፌጦ እና በሎሚ እንጀራ ፍትፍት በባዶ ሆድ መጉረስ ነው።

Äthiopien | Vorbereitungen für die Neujahresfeier
ምስል፦ DW/Y. Gebregziabher

በኢትዩጵያ የተለያዩ በአላትእንደየ ባህሉ እና እምነቱ በድምቀት ይከበሩባታል።  በአዲስ አመት ጠዋት  በባዶ ሆድ  ፌጦ ለምን ይበላል ጥቅሙስ ምንድነው ስንል ሁለት ሰዎችን አናግረናል ።

ደራሲ ወ/ሮ ፀሀይ መላኩ ፌጦ ለምን ለአዲስ አመት እንምንበላ እና ጥቅሙስ ምንድነው ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄ ተከታዩን ምላሽ ሰተውናል 

«  እኛ ኢትዩጵያውያን በአዲስ አመት ስናከብር ለየት ያለ ባህልና ስርአቶችን አሉን ከነዚ ውስጥ አንዱ ጠዋት ተነስቶ በቀዝቃዛ ውሀ ገላን መታጠብ ከዛ መልስ በፌጦ እና በሎሚ እንጀራ ፍትፍት በባዶ ሆድ መጉረስ ነው። ቤተሰቡ በሙሉ ይጎርሳል»  ሲሉ  ስለ ፌጦ ጥቅም ምንድነው ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄ  «ፌጦ በተፈጥሮው ባክቴሪያ ወይም ቫይረስን መከላከል የሚችል አቅም ያለው ነው ሎሚ እንደዚሁ ሁለቱን ቀላቅሎ ፈትፍቶ በብላት ሆድ ውስጥ ያለውን ተውሳክ ሆድ ውስጥ የማይመች ነገር ለማስወገድ የሚያግዝ  ነው። አመቱን በሙሉ ጤነኛ ሆኖ  አዲሱን አመት እንዲያሳልፈን የመልካም ምኞት መግለጫም እንዲሁም ድርጊትም ነው » ብለዋል 
ወ/ሮ አሰገደች ዘገየ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ናቸው ፌጦ እና አዲስ አመትን ያላቸውን ግንኙነት ጠይቀን 
«ፌጦ የሚበላው በአዲስ  አመት ነው።  እናቶቻችን የሆድ በሽታ ካለ ያድናል ይላሉ። ፌጦ የእንቁጣጣሽ ለታ አንድ ሰአት ነው የሚበላው። ፌጦን ለአዲስ አመት መብላት እምነት ሳይሆን ባህል ነው»ብለዋል ቀጥለውም ፌጦ ፍትፍት እንዴት እንደሚዘጋጅ ላቀረብንላቸው ጥያቄ «መጀመሪያ ፌጦ ፀሀይ ይሰጣል ከዛ ይወቀጣል ትንሽ ውሀ ጠብ ተደርጎ በሎሚ በእንጀራ ይፈተፈታል» ቀጥለውም  ፍትፍቱን  በእለቱ መላው ቤተሰቤን ሶስት ሶስት ግዜ አጎርሳለሁ ብለዋል ። «ዶሮ ፣ ቡና፣ ዳቦ የመሳሰሉት ዝግጅቶች ከፌጦ በውሀላ ነው» ብለዋል ።

ማህሌት ፋሲል

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW