ፓሪስ ላይ የተካሄደዉ የጀርመን ፈረንሳይ ትብብር ጉባኤ
ዓርብ፣ ኅዳር 12 2018
ማስታወቂያ
ፓሪስ ላይ የተካሄደዉ የጀርመን ፈረንሳይ ትብብር ጉባኤ
ባለፉት ዓመታት በቀጠለዉ የሩሲያ ዩክሬይን ጦርነት፤ የኃይል እና ቴክኖሎጂ ጥገኝነት በአዉሮጳና አሜሪካ ማለትም የትራንስ አትላንቲክ ትስስር ጥንካሬ እየላላ መምጣት እና አስተማማኝ አለመሆን ፤ ብሎም የፖለቲካ አለመረጋጋት፤ የአዉሮጳ ዋንኛ አንቀሳቃሽ ሞተር ለሆኑት ለፈረንሳይ ጀርመን ትብብር ፤ ጫና ዉስጥ ሊከተዉ መቻሉ ተነግሯል። ይህን የፈረንሳይ ጀርመን ትብብርን ለማጠናከር ደግሞ፤ ከመቼዉን ጊዜ በላይ አስፈላጊ እና አፋጣኝ እርምጃ መወሰድ እንዳለበትም እየተነገረ ይገኛል። አዉሮጳ በኢኮኖሚ በኢንዱስትሪ በቴክኖሎጂ ብቻ ሳይሆን በወታደራዊ እና ደህንነት ጊዳዮች ረገድ፤ ልዑዋላዊነትዋን በአስቸኳይ ማጠናከር አስፈላጊ የሆነበት ደረጃ ላይ መድረስዋን የፈረንሳይ ዓለም አቀፍ ግንኙነት ተቋም በፓሪስ ላይ በአዘጋጀዉ የሁለቱ ሃገራት ትብብር ወቅታዊ ጉዳዮችን በዳሰሰዉ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ በባለሞያዎቹ አፅኖት ተሰጥቶበታል። ወቅቱም አዉሮጳ በወታደራዊ እና ደህንነት ጉዳዮች እንዲሁም በሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን ሃገሮች ትስስር «በኔቶ» የወደፊት እጣ ፈንታ ላይም ከዩናይትድ ስቴትስ ጥገኝነት ዉጭ ቆም ብላ፤ ማሰብ የምትጀምርበት ምዕራፍ ላይ መድረስዋም ተመላክቷል።
ሃይማኖት ጥሩነህ
አዜብ ታደሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ