1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጥፋተኞች የተባሉ ታስሯል አልያም ከስራ ታዷል

ቅዳሜ፣ ጳጉሜን 4 2015

ብዙዎች ፓስፓርት ለማውጣትም ሆነ ለማደስ በደላሎች ማታለል ተፈጽሞባቸዋል። እስከ 150 ሺህ ብር በሙስና እየተጠየቁ ፓስፓርት ተሰርቶላቸው ከሀገር የወጡ ሰዎች ስለመኖራቸው ያንን የሚያውቁ ገልፀውልናል።

የኢትዮጵያ ፓስፖርት
ፓስፖርት ለማውጣትና ለማሳደስ በተቋሙ ሰራተኞች ጉቦ እንደሚጠየቁ ተገልጋዮች በምሬት ይገልጻሉ። ተቋሙ በቅርቡ ሙስና ፈጽሟል ያላቸውን ሰራተኞቹ ወደ ህግ የማቅረብ ስራ ማከናወኑን ገልጿል።ምስል DW/E. B. Tekle

ፓስፖርትን በጉቦ

This browser does not support the audio element.

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ከፓስፓርት እድሳት እና አሰጣጥ ጋር ተያይዞ ሕዝብን ያማረሩ ሰራተኞቹን ማገዱን እና ከሥራ ማሰናበቱን አስታወቀ። 
አገልግሎቱ አሁን በየሳምንቱ ፓስፖርት እየታተመ እየገባ መሆኑን የገለፀ ሲሆን በተለይ ወደ አረብ ሀገራት ለሚሄዱ ዜጎች ቅድሚያ ተሰጥቶ እየታተመ መሆኑን  በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። 
የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት የሚሰጠው የፓስፖርት አገልግሎት ኢትዮጵያዊያን በብርቱ ከሚማረሩባቸው የአገልግሎት ዘርፎች ዋነኛው መሆኑን ይታወቃል።

ከፍተኛ እንግልት የሚስተዋልበት የኢሚግሬሽን አገልግሎት

ሌሊት መሰለፉ፣ እንግልቱ፣ ማመናጨቁ ፣ ወረፋ መጠበቁ የዚህ አገልግሎት ፈላጊዎች የየ ዕለት ዋነኛ የሮሮ መነሻዎች ናቸው። ይህ በአብዛኛው ህዝብ ዘንድ የሚታወቅ ቢሆንም ተቋሙ ይህንን በትክክል እንደሚያምን  በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ምን ያህል እንደሆኑ ባይገልፁም የታገዱ፣ የታሰሩ የተቋሙ ሠራተኞች አሉ። ብለዋል።
"መሥሪያ ቤቱ በርካታ የሌብነት ኔትዎርክ ያለበት ነው። ደላሎች በጣም በስፋት በውጭም በውስጥም ተንሰራፍተውበታል። ይሰሩበታል። ከዚህ ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎችን የማገድ፣ እንደዚሁም ደግሞ እጅ ከፈንጅ ከነማስረጃ የተገኙትን ደግሞ የማሰር እንደዚሁም ምርመራ እንዲካሄድባቸው የማድረግ ሥራዎችን ስንሠራ ቆይተናል። በርካታ ሰዎች በዚህ ችግር ውስጥ ወድቀው ተገኝተዋል"

ፓስፓርት ለማደስና ለማውጣት የሚጠየቀው ጉቦ

ብዙዎች ፓስፓርት ለማውጣትም ሆነ ለማደስ በደላሎች ማታለል ተፈጽሞባቸዋል። እስከ 150 ሺህ ብር በሙስና እየተጠየቁ ፓስፓርት ተሰርቶላቸው ከሀገር የወጡ ሰዎች ስለመኖራቸው ያንን የሚያውቁ ገልፀውልናል። ያነግልገርናት አንድ ለስድስት ወራት ፓስፓርት ለማደስ የተንገላታች ሴት በግልጽ በተቋሙ ሰራተኞች ጉቦ እንደሚጠየቅ እና ከፍተኛ ገንዘብ እየከፈሉ ይህንን አገልግሎት የሚያገኙ መኖራቸውን ገልፃለች።
"ስጥ ላይ የሚሠሩ ሰዎች የበፊቱን ፋይልህን አውጥተው ፣ አትመው ቤት ድረስ በሞተር ያደርሱልሃል ሠላሳ እና አርባ ሺህ ብር እየተቀበሉ። ግን ሀሰተኛ ነው አይሰራም" 

ተቋሙ የደረሰበት ዜጎችን ያማረረው ብልሹ አሠራር

ይህ በተቋሙ ኃላፊ የተረጋገጠ ወንጀል መሆኑም ተግልጿል።
"ለምሳሌ የገንዘብ መቀበያ ሰነድ የሚሸጡ በርካታ ሰዎችን  በቁጥራቸው ይዘናል። የኢሚግሬሽንን ሰነዶች በማስመሰል እና ቅድሚያ ታገኛላችሁ የሚል አውጭ አለ። ከዛ ውጪ ከውስጥ ያገኘናቸው የውስጥ ሰነዶችን ከውጪ ደላሎች ጋር በመነጋገር የውስጥ ሰነዶችን አሳልፎ የመስጠት ሥራዎች ናቸው" 

የአገልግሎቱን ጥራት አሻሽለ‍ኣለሁ፣ የዜጎችን እንግልት አፈታለሁ የሚለው የኢሚግሬሽን እና የዜግነት አገልግሎት በተለይ ወደ አረብ ሀገራት ለሚሄዱ ዜጎች በርከት ያለ ፓስፓርት ታትሞ እየገባ መሆኑንም አስታውቋል።

ሰሎሞን ሙጬ

ዮሃንስገብረእግዚአብሄር

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW