ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በፈረንሣይ
ሰኞ፣ ሚያዝያ 15 2004ማስታወቂያ
ለፕሬዚደንታዊው ምርጫ በዕጩነት ከቀረቡት አሥር ዕጩዎች መካከል አንዱም ለከፍተኛው የሀገሪቱ ሥልጣን የሚያበቃውን የመራጭ ድምፅ ባለማግኘቱ እአአ የፊታችን ግንቦት ስድስት ቀን በፍራንስዋ ኦሎንድ እና በኒኮላ ርኮዚ መካከል የመለያው ሁለተኛ ዙር ምርጫ ይካሄዳል። በፕሬዚደንታዊው ምርጫ ላይ በተለይ በማሪን ለ ፔን የሚመራው የቀኝ አክራሪው ፓርቲ 17,9 ከመቶ የመራጭ ድምፅ በማግኘት የሶስተኛነቱን ቦታ መያዙና በምርጫው የተሳተፈው መራጭ ሕዝብ ቁጥር ከሰማንያ ከመቶ በልጦ መገኘቱ ብዙዎችን አስገርሞዋል። የግራ ፓርቲ መሪ ዦን ሉክ ሜሎንሾ 11,1ከመቶ ፣ የዴሞክራቲክ ፓርቲ መሪ ፍራንስዋ ባይሩ ደግሞ 9,1ከመቶ የመራጭ ድምፅ አግኝተዋል። በፕሬዚደንታዊ ምርጫ ሂደት አኳያ ባጠቃላይ ስለታየው የሀገሪቱ ሕዝብ አስተያየት የፓሪስዋ ወኪላችን ሀይማኖት ጥሩነህ ስቱድዮ ከመግባታችን በፊት ቀጣዩን ማብራሪያ በስልክ ሰጥታኛለች።
ሀይማኖት ጥሩነህ
አርያም ተክሌ