1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ፕሮፌሰር መረራ ውዝግብ ስለገጠመው ጽሁፋቸው ምን ይላሉ?

ቅዳሜ፣ ነሐሴ 23 2012

“ርዕሱን እኔ አልመረጥኩም” ያሉት ፖለቲከኛው  የጽሁፉ ርዕስ የተሰጣቸው ሃምሌ 22 ቀን 2012 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በተደረገው የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ውይይት ሰባት ሰዎች በብሔራዊ መግባባትና ሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ ያተኮሩ የመነሻ ሃሳቦች ቀርበው በቀጣይነት ውይይት እንዲደረግባቸው ሲወጠን መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

Pro Merera Gudina vorsitzender OFECO
ምስል፦ DW/S. Wegayehu

ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና በአነጋጋሪው ጥናታቸው ተጸጽተው ይሆን?

This browser does not support the audio element.

ፕሮፌሰር መረራ ውዝግብ ስለገጠመው ጽሁፋቸው ምን ይላሉ

ነሃሴ 16 ቀን 2012 ዓ.ም. በሀገር ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ላይ በማተኮር ተካሂዶ የነበረው የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮችን ባሳተፈው መድረክ ላይ የቀረበው የፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ጥናታዊ ፅሁፍ በሳምንቱ አነጋገሪ ከነበሩ ጉዳዮች ይጠቀሳል፡፡

የብሔራዊ መግባባት ታሪካዊ ዳራዎች የሚል ስያሜ የተሰጠው «ጥናቱ» ሲቀርብ “ሃገራዊ አንድነትን ጥያቄ ውስጥ የሚያሰገባ” የሚል አስተያየትን በወቅቱ አሰጥቶ ነበር።

ጥናታዊ ጽሁፉን አስመልክቶ የተጠየቁት ፕሮፈሰር መረራ ጉዲና ለማለት የፈለጉትና በመገናኛ ብዙሃን ላይ ጎልቶ የወጣው ሃሳብ ልዩነት እንዳለው ነው የሚሞግቱት፡፡ “ርዕሱን እኔ አልመረጥኩም” ያሉት ፖለቲከኛው  የጽሁፉ ርዕስ የተሰጣቸው ሃምሌ 22 ቀን 2012 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በተደረገው የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ውይይት ሰባት ሰዎች በብሔራዊ መግባባትና ሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ ያተኮሩ የመነሻ ሃሳቦች ቀርበው በቀጣይነት ውይይት እንዲደረግባቸው ሲወጠን መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

የዘመናዊት ኢትዮጵያ የታሪክ ዳራዎችን እና የሃገረ መንግስት ግንባታ ፈተናዎችን ከነገስታቱ እስከ የአሁኑ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ መንግስታዊ አስተዳደር ድረስ በጽሁፋቸው መቃኘታቸውን የሚያነሱት ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ችግሮች ናቸው ብለው ለጠቀሷቸው ነጥቦችም መፍትሄ ይሆናል ያሉትን ማስቀመጣቸውን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ታሪክ የመገዳደልና የመጠላለፍ አካሄድ ነበር ያሉት ፕ/ር መረራ ከዚያ መማር የሚያስችል በዋልታ ረገጥ የተወጠሩ ሃሳቦችን ወደ መሃል ለማምጣት መወያየት መሆኑን ይጠቁማሉ፡፡ የመገዳደል ታሪክ ኢትዮጵያ ሰፊ እድል እንዲያመልጧት ከማድረጉም በላይ አሁን ላይ “የዓለም ጭራ አደርጓታል” ብለዋል። ኢትዮጵያን ገጥሟታል ባሉት የታሪክ ዳራዎች ላይ ከሃገር ውስጥ እና ከሃገር ውጭ ስለ ኢትዮጵያ የተጻፉ መጽሃፍትን በማጣቀሻነት ተጠቅመውም ነበር።

ውይይቱን ተከትሎ ስለምን አጨቃጫቂ ነጥቦች ተነሱ፤  ለብሔራዊ መግባባትስ ይጠቅም ይሆን ብለን ለጠየቅናቸው ጥያቄም “ብዙዎች አልተረዱኝም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ስዩም ጌቱ

ታምራት ዲንሳ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW