የተዋጣው ገንዘብ የት ገባ?
ዓርብ፣ ጥር 16 2017
ማስታወቂያ
የትግራይ ዳያስፖራ ማሕበራት የገለልተኝነት ጥያቄ
በአውሮፓና ሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ማሕበራት በርካታ አወንታዊ ተግባራት መፈጸማቸው ቢነገርላቸውም የዚያኑ ያህል በበርካታ ጉዳዮች ይወቀሳሉ። አንዱ የሚወቀሱበት ነጥብ ከፖለቲካ ወገንተኝነት አልጸዱም የሚል ነው። በተለያዩ ጊዜያት የሚያዘጋጇቸው መድረኮችም የክልሉ ገዢ ፖርቲ ህወሓትን ለማስደሰት ሲባል የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ያገላሉ በሚል ይተቻሉ ።የትግራይ የተቃዋሚ ፓርቲዎችበውጭ አገራት የሚሳተፉባቸው መድረኮች እንዳይሳኩ እንቅፋቶች መፍጠርና የመሳሰሉት ችግሮችም እንደሚስተዋልባቸው ይነገራል።
ሌላው ዐቢይ ችግር ተብሎ የሚጠቀሰው ደግሞ፦ በጦርነቱ ወቅት የተዋጣው በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላርና ዩሮ የት ገባ? የሚል ነው። ይህ ጥያቄ በተለያዩ መድረኮች ቢነሳም ጠብ የሚል ምላሽ እንዳልተገኘ ያነጋገርናቸው የማሕበረሰቡ አባላት በምሬት ይገልጻሉ። በጀርመን ሙኒክ ከተማ የሚኖሩና የትግራይ ማሕበረሰብ በሚመለከቱ ጉዳዮች ንቁ የፖለቲካ ተሳትፎ የሚያደርጉት ፕሮፌሰር መድሃኔ አስመላሽን በነዚህ ጉዳዮች እንግዳ አድርገናቸዋል። መሉ ቃለ ምልልሱን ለማድመጥ የድምፅ ማዕቀፉን ይጫኑ።
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
ማንተጋፍቶት ስለሺ