1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ኅብረተ ሰብሰሜን አሜሪካ

ፕሮፌሰር ገቢሳ እጀታ ከፕሬዚደንት ጆ ባይደን እጅ ሜዳይ ተሸለሙ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 14 2016

ትውልደ ኢትዮጵያዊ አሜሪካዊው ታዋቂው ፕሮፌሰር ገቢሳ እጀታ ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን እጅ የሀገሪቱን ብሔራዊ የሳይንስ ሜዳይ ሽልማት ትናንት ማምሻውን ተቀብለዋል ። ፕሮፌሰር ገቢሳ ለሽልማት ያበቃቸው በሰብል ዘረ መል ምርምር ላይ ላበረከቱት ላቅ ያለ የምርምር ውጤት መሆኑም ተገልጧል ።

ፕሮፌሰር ገቢሳ እጀታ እና የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን
ፕሮፌሰር ገቢሳ እጀታ ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን እጅ የሀገሪቱን ብሔራዊ የሳይንስ ሜዳይ ሽልማት ትናንት ማምሻውን ተቀብለዋል ምስል፦ Ron Sachs/Zuma/IMAGO

ቀደም ሲል አምስት ሚሊዮን ዶላር ከቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ግብረ-ሰናይ ድርጅት አሸንፈዋል

This browser does not support the audio element.

ትውልደ ኢትዮጵያዊ አሜሪካዊው ታዋቂው ፕሮፌሰር ገቢሳ እጀታ ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን እጅ የሀገሪቱን ብሔራዊ የሳይንስ ሜዳይ ሽልማት ትናንት ማምሻውን ተቀብለዋል ። ፕሮፌሰር ገቢሳ ለሽልማት ያበቃቸው በሰብል ዘረ መል ምርምር ላይ ላበረከቱት ላቅ ያለ የምርምር ውጤት መሆኑም ተገልጧል ።

ፕሮፌሰር ገቢሳ እጀታ በተለይ በማሽላላይ ያደረጉት ጥናት ቀደም ሲልም ለተደጋጋሚ ሽልማት አብቅቷቸው ነበር ። ዋና ዋናዎቹን ለመጥቀስ ከ14 ዓመታት በፊትም የዓለም የምግብ ሽልማትን አሸንፈዋል ። ጥገኛ አረምን መቋቋም የሚችሉ ዝርያዎችን ለማዳቀል ለሚያካሂዱት ምርምር ደግሞ ከአምስት ዓመታት በፊት አምስት ሚሊዮን ዶላር ከቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ማሸነፋቸውም አይዘነጋም ።

ፕሮፌሰር ገቢሳ ማሽላን የሚያጠቃ ጥገኛ አረም ዘረ-መል ላይ ለረዥም ጊዜያት ከፍተኛ ምርምር በማድረግም ይታወቃሉ ። ለመሆኑ ፕሮፌሰር ገቢሳ ትናንት ከፕሬዚደንት ጆ ባይደን የተቀበሉት ሽልማት ከሌላው ለየት የሚያደርገው ምንድን ነው? የዋሽንግተን ወኪላችን አበበ ፈለቀን ከፍተኛ ደረጃ የያዘ መሆኑን ገልጧል ።

ሽልማቱ እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር ከ1959 ዓ.ም ጀምሮ በአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ ሲሰጥ የቆየ ሽልማት ነው ። በየዓመቱ ተሸላሚዎቹ በፕሬዚደንቱ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ መማክርት ጉባኤ የሚመረጡ ታላቅ እና ምርጥ የሚባሉ ሳይንቲስቶች ለሽልማት ይበቃሉ ። ዘንድሮ በሳይንስ ዘርፍ ከተመረጡ 9 ሳይንቲስቶች መካከል ፕሮፌሰር ገቢሳ እጀታ አንዱ መሆን ችለዋል።      

ፕሮፌሰር ገቢሳ እጀታ በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን የሀገሪቱ ብሔራዊ የሳይንስ ሜዳይ ሜዳይ ሲሸለሙምስል፦ Jacquelyn Martin/AP/picture alliance

የዛሬ አምስት ዓመት ፕሮፌሰር ገቢሳ አምስት ሚሊዮን ዶላር ሲሸለሙ ከአራት ዓመታት በኋላ በድሀ አገሮች የሚገኙ ወጣት የሥራ ፈጣሪዎች አረምን መቋቋም የሚችሉ የማሽላ ዝርያዎችን በስፋት ለማምረት ይችላሉ የሚል ተስፋም ሰንቀውም ነበር ። ከዚያን ሽልማት በኋላ ስድስት ዓመታት ተቆጥረዋል ። አሁን ያገኙት ሽልማት ለሌሎች በምግብ እጥረት ለሚሰቃዩ የአፍሪቃ ደሀ ሃገራት በተለይ ደግሞ በየክልሉ የረሐብ አደጋ የሰዎችን ሕይወት በተደጋጋሚ ለሚቀጥፍባት እና አሁንም በተለያዩ ቦታዎች የረሀብ አደጋ ለተደቀነባት ኢትዮጵያውያንስ ምን ፋይዳ ይኖረዋል? አበበ ጥያቄዎቹን ያብራራል ። ሙሉ ቃለ መጠይቁን ከድምፅ ማቀፉ ማድመጥ ቻላል ። 

አበበ ፈለቀ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW