1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ፖለቲካዊ ቀዉስ በጀርመን

ሰኞ፣ የካቲት 2 2012

የጀርመንዋ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል እንዲተኳቸዉ የመረጥዋቸዉ የክርስቲያን ዴሞክራት ሕብረት ፓርቲ(CDU) ሊቀመንበር ክራምፕ ካርንባወር ሀገሪቱ በቅርቡ በምታካሂደው የምክር ቤት ምርጫ በእጩነት እንደማይቀርቡ ተናገሩ። የ 57 ዓመትዋ የጀርመን መከላከያ ሚኒስትር ለመራሂተ መንግሥትነት አንጌላ ሜርክል የቅርብ ሰው ነበሩ።

Kanzlerin Merkel und AKK Mimik
ምስል፦ picture-alliance/dpa/C. Soeder

የጀርመንዋ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል እንዲተኳቸዉ የመረጥዋቸዉ የክርስቲያን ዴሞክራት ሕብረት ፓርቲ(CDU) ሊቀመንበር ክራምፕ ካርንባወር ሀገሪቱ በቅርቡ በምታካሂደው የምክር ቤት ምርጫ በእጩነት እንደማይቀርቡ ተናገሩ።  የክርስቲያን ዴሞክራት ሕብረት (CDU) ሊቀመንበር እና የጀርመን መከላከያ ሚኒስቴር የሆኑት ፖለቲከኛ ይህን በማድረጋቸዉ በጀርመን ፖለቲካ መድረክ ግርምታን ፈጥሯል። መገናኛ ብዙኃንም የጀርመኑ የክርስትያን ዴሞክራት ፓርቲ ቀውስ ላይ ይገኛል ሲሉ እየዘገቡ ነው። ጀርመናዊትዋ ፖለቲከኛ ፓርቲያቸውን ወክለው ለመራሂተ መንግሥትነት እንደማይወዳደሩ በይፋ ሲናገሩ ከፓርቲ ሊቀመንበርነቱም እንደሚለቁ አመልክተዋል። ይሁንና ካርንባወር ፓርቲው ሊቀመንበር እስኪያገኝ የፓርቲው መሪ ሆነው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። የመከላከያ ሚኒስቴር ኃላፊነታቸውንም እንዲሁ።   

ምስል፦ picture-alliance/dpa/B. von Jutrczenka

« በመራሂተ መንግሥት ምርጫ ላይ በእጩነት አልቀርብም ።  ፓርቲውን ወክሎ ለመራሄ መንግሥትነት የሚቀርብ እጩ እስኪገኝ ድረስ በመሪነት ቦታዬ እቀጥላለሁ። እንደኔ አመለካከት የፓርቲው ሊቀመንበርነት ቦታና ፓርቲውን ወክሎ ለመራሄ መንግሥትነት በእጩነት የሚቀርበዉ ግለሰብ አንድ መሆን አለበት። በዚህም ምክንያት ለመራሄ መንግሥት በእጩነት የሚቀርብ እስኪገኝ ድረስ የፓርቲው ሊቀመንበር ሆኜ አገለግላለሁ። ፓርቲው ስብሰባ አድርጎ በእጩነት የሚቀርበው ሰው ሲገኝ ግን የፓርቲ ሊቀመንበርነቱን ቦታም አስረክባለሁ። የመከላከያ ሚኒስቴርነት ስልጣኔን ደግሞ በመራሂተ መንግሥትዋ ፍላጎትና ምኞት መሰረት እንዳገለግል እስከተመረጥኩበት የመጨረሻ ቀን ድረስ እቀጥላለሁ። »  
  
በጎርጎረሳዊው 2018 ዓ.ም የክርስቲያን ዴሞክራት ሕብረት ፓርቲ(CDU) ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት የ 57 ዓመትዋ የጀርመን መከላከያ ሚኒስትር ክራምፕ ካርንባወር፤ በጎርጎረሳዊው 2021 ዓመት በጀርመን በሚካሄደዉ የፓርላማ ምርጫ ለመራሂተ መንግሥትነት አንጌላ ሜርክል ያጭዋቸው ቅርብ ሰው ነበሩ።  ሜርክል ፤ ለፓርቲያቸው ሊቀመንበርነትም ሆነ ለሀገሪቱ መራሂተ መንግሥትነት ያጭዋቸዉ ፖለቲከኛ እዚህ ዉሳኔ ላይ በመድረሳቸዉ እንደተፀፀቱ ተዘግቧል። 

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW