1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፖለቲካ ምህዳሩ የጠበባት እና ሰላማዊ ትግል የታገደባት ትግራይ ክልል

ዓርብ፣ መስከረም 11 2016

በትግራይ የፖለቲካ ምህዳሩ እየጠበበ፥ ሰላማዊ ፖለቲካዊ ትግል ማድረግ አስቸጋሪ አድርጎት እንዳለ በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለፁ። ከጠሩት ሰልፍ ጋር በተገናኘ ታስረው በቅርቡ ከእስር በዋስትና የተለቀቁት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች በክልሉ ለውጥ ለመፍጠር ትግላቸው አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አንስተዋል።

መቐለ ከተማ፤ ትግራይ
መቐለ ከተማ፤ ትግራይምስል EDUARDO SOTERAS/AFP

«የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር በሚድያ ባለሙያዎች ላይ የተፈፀመው እንግልት እንዲያጣራ፥ ይህ በፈፀሙት ላይም ተጠያቂነት እንዲያረጋግጥ ጥሪ ቀርቧል»

This browser does not support the audio element.

በትግራይ ክልል የፖለቲካ ምህዳሩ እየጠበበ፥ ሰላማዊ ፖለቲካዊ ትግል ማድረግ አስቸጋሪ አድርጎት እንዳለ በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለፁ። ከጠሩት ሰልፍ ጋር በተገናኘ ታስረው በቅርቡ ከእስር በዋስትና የተለቀቁት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች በክልሉ ለውጥ ለመፍጠር ትግላቸው አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አንስተዋል። በሌላ በኩል ባለፈው ጳጉሜ ሁለት በመቐለ ከተደረገው እና በፓሊስ በሐይል ከተበተነው ሰልፍ ጋር በተገናኘ መግለጫ ያወጣው የጋዜጠኞች መብት ተሟጓቹ ሲፒጄ፥ በትግራይ በሚድያ ባለሙያዎች ላይ እስር፣ ድብደባ፣ እንግልት እንዲሁም ሌሎች ሕገወጥ ተግባራት መፈፀማቸው አስታውቋል።በመቀሌ በሰላማዊ ሰልፍ ቅስቀሳ ላይ የነበሩ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ታሰሩ

ባለፈው ጳጉሜ 2 ቀን 2015 ዓመተምህረት በትግራይ በሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመቐለ ተጠርቶ በፖሊስ በሐይል ከተበተነው ሰልፍ ጋር በተገናኘ ትላንት መግለጫ ያወጣው የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ሲፒጄ፥ በመቐለ ሮማናት አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ለመዘገብ በተገኙ የሀገር ውስጥ እና ውጭ ሚድያ ጋዜጠኛ እስር፣ ድብደባ፣ እንግልት፣ ስራቸው እንዳይከውኑ የማገድ እና ሌሎች ተግባራት መፈፀማቸው መረጃዎች እንደደረሱት አስታውቋል። የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር በዕለቱ በሚድያ ባለሙያዎች ላይ የተፈፀመው እንግልት እንዲያጣራ፥ ይህ በፈፀሙት ላይም ተጠያቂነት እንዲያረጋግጥ ጥሪ ያቀረበው ሲፒጄ፥ በተቃዋሚዎች ሰልፍ ጨምሮ በሁሉም አጋጣሚዎች የፕረስ ነፃነት ሊከበር ይገባልም ብሏል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በወቅታዊ የትግራይ የፖለቲካ ጉዳዮች ዙርያ ማብራርያ የሰጡት በቅርቡ ከእስር የተፈቱ የትግራይ ነፃነት ፓርቲ፣ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ እና የባይቶና አመራሮች በትግራይ ያለው የፖለቲካ ምህዳር ይበልጥ እየጠበበ ሰላማዊ ትግል ማድረግ ወደማይቻልበት ሁኔታ እያመራ ስለመሆኑ ገልፀዋል። ከሰልፉ ጋር በተገናኘ ታስረው በኃላ በፍርድቤት ውሳኔ በዋስ የተለቀቁት የትግራይ ነፃነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር ደጀን መዝገቡ በትግራይ ስላለው ፖለቲካዊ ምህዳር ማብራርያ ሲሰጡ ለሰላማዊ የፖለቲካ ትግል የማይመች ብለውታል።

መቐለ ከተማ፤ ትግራይ ምስል Million Hailesilasse/DW

ትግራይ ክልል ተጨማሪ የተቃዋሚዎች እስር

ከዚህ በተጨማሪ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮቹ በትግራይ ፖለቲካ የወታደራዊ መሪዎች አልያም ጀነራሎች ተሳትፎ አሉታዊ ሚና እየፈጠረ መሆኑ ይገልፃሉ። የሳልሳይ ወያነ ትግራይ ሊቀመንበር አቶ ሃያሉ ጎደፋይ፥ በትግራይ ያሉ ወታደራዊ መሪዎች ለአንድ ፓርቲ ያላቸው ውግንና ትክክል እንዳልሆነ የሚያነሱ ሲሆን በዚህ የሚቀጥሉ ከሆነ ህወሓት ላይ የምንይዘው አቋም በወታደራዊ መሪዎቹ ላይም የሚሰራ ይሆናል ብለዋል።ስርቆት፣ ዘረፋ፣ እገታና ሥርዓተ አልበኝነት በትግራይ

በትግራይ ዝርፍያ፣ ሕገወጥነት የመብት ጥሰት ተባብሶ ቀጥሏል የሚሉት እነዚህ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች የትግራይ ህዝብ የፍትህ፣ የመብት፣ የተጠቃሚነት እና ዴሞክራሲ ጥያቄዎች እስኪመለሱ ድረስ ሰላማዊ ትግሉ እንደሚቀጥልም ገልፀዋል። አቶ ሃያሉ ጎደፋይ

በየጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅቱ ሲፒጄ ሪፖርት እንዲሁም ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በሚነሱ ጥያቄዎች ዙርያ ከክልሉ ግዚያዊ አስተዳደር ምላሽ ለማግኘት በተደጋጋሚ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW