108ኛው ፓርቲ ተመሠረተ
ማክሰኞ፣ መጋቢት 17 2011ማስታወቂያ
የሚከተለው የፓለቲካ አቅጣጫ ወግ አጥባቂ ለዘብተኛ መሆኑን ያመለከተው አዲሱ ፓርቲ እስካሁን ያልተፈቱ ውስብስብ ችግሮችን አካታች እና ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ከሌሎች ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመሆን በጋራ እንዲፈቱ እንደሚሠራም አስታውቋል። በአሁኑ ሰአት መንግሥት ከብዛት ይልቅ ሰብሰብ ብላችሁ ጠንካራ ፓርቲ በማዋቀር ተንቀሳቀሱ በሚልበት ወቅት ተጨማሪ የመመስረቱን ተገቢነት የተጠየቀው ፓርቲ፣ የመደራጀት መብትን መንግሥት እስካልገደበ ድረስ ችግር እንደሌለው ነው የገለጸው። በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጡ የፖለቲካል ሳይንስ እና አለም አቀፍ ግንኙነቶች ምሁር የፖለቲካ ፓርቲዎች ሃሳቦችንና አመለካከቶችን ማሰባሰብ ቢኖርባቸውም ከዚህ በተቃራኒ መሆናቸውን፤ ይህም የተቋማት ግንባታ እና የመሪዎች ሰብእና አለመጠናከር ነጸብራቅ መሆኑን አመልክተዋል። ከአዲስ አበባ ዘጋቢያችን ሰሎሞን ሙጬ ዝርዝሩን ልኮልናል።
ሰሎሞን ሙጬ
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ