ታሪክኢትዮጵያ
129ኛው የአድዋ ድል በዓል እንዴት ይታወሳል?
ቅዳሜ፣ የካቲት 22 2017
ማስታወቂያ
129ኛው የአድዋ ድል በዓል ነገ እሑድ የካቲት 23 ቀን 2017 ዓ. ም በአዲስ አበባ ፒያሳ በሚገኘው የድሉ መታሰቢያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይከበራል።
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በበዓሉ አከባበር ላይ በሚታዩ አለመግባባቶች ምክንያት የበዓሉ ማክበሪያ ስፍራ የተለያየ ቦታ ሲሆን ተስተውሏል፣ ግጭቶችና ልዩነቶችም ተስተውለዋል። ካለፈው ዓመት ወዲህ በዓሉን በዋናነት መከላከያ ሚኒስቴር ማስተባበርም ጀምሯል።
በዚህ ዓመት በዓሉ በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም የሚከበር በመሆኑ ሕዝብ አደባባይ ወጥቶ የሚያከብርበት እድል ያለ አይመስልም።
ይህንን ታላቅ የነጻነት እና የአንድነት በዓል ለማክበር እውን ይህ ትውልድ የድሉን መንፈስ መሸከም ይችላልን? ድሉንስ የእኔ ነው ብሎ ሊያከፍብር የሚያስችለውን አንድነት፣ ሕብረት እና መተሳሰብ አዳብሯልን? ይህንን በተመለከተ ጥቂት አስተያየቶችን አሰባስበናል።