1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

13 ሚሊዮኖችን ለረሐብ ያጋለጠው ድርቅ

ማክሰኞ፣ የካቲት 1 2014

በአፍሪቃ ቀንድ ቀጣና በሚገኙ ሦስት አገራት የተከሰተው እና አስከፊ ጉዳት ያደረሰው ድርቅ 13 ሚሊዮን ሰዎችን ለከፋ የረሃብ አደጋ አጋልጧል ተባለ። የዓለም ምግብ መርኃ ግብር እንዳስታወቀው በኬንያ ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ የሰብአዊ ቀውስ ከማስከተሉ በላይ እንስሳትም በውኃ እና ግጦሽ እጦት እንዲሞቱ ሰበብ ኾኗል።

Äthiopien | Dürre in Borena
ምስል፦ Firaol Wako/PHD

የተከሰተው ድርቅ ከባድ ጫና እያሳደረ ነው ተብሏል

This browser does not support the audio element.

በአፍሪቃ ቀንድ ቀጣና በሚገኙ ሦስት አገራት የተከሰተው እና አስከፊ ጉዳት ያደረሰው ድርቅ 13 ሚሊዮን ሰዎችን ለከፋ የረሃብ አደጋ አጋልጧል ተባለ። የዓለም ምግብ መርኃ ግብር እንዳስታወቀው በኬንያ ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ የሰብአዊ ቀውስ ከማስከተሉ በላይ እንስሳትም በውኃ እና ግጦሽ እጦት እንዲሞቱ ሰበብ ኾኗል። ተቋሙ በኢትዮጵያ በተለይም በኦሮሚያ፣ በሶማሌ እና በደቡብ ክልሎች በተከሰተው ድርቅ አስቸኳይ የምግብ ርዳታ ለሚሹ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች የምግብ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጾ፤ ሆኖም ተጨማሪ ገንዘብ እንደሚያስፈልገውም ዐስታውቋል። የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን በኢትዮጵያ አሁን የተከሰተው ድርቅ ከባድ ጫና ያሳደረ እና ከዓመታት በፊት ቆላማና አርብቶ አደር ነዋሪዎች ይኖሩባቸው በነበሩ አካባቢዎች የተከሰተውን የሚመስል እንደሆነ ገልጧል። ዋናው የችግሩ ምንጭም ወቅቱን ጠብቆ እንዲዘንብ ይጠበቅ የነበረብ ዝናብ አለመዝነቡና የአየር ንብረት ለውጥ ነው ተብሏል።

ሰለሞን ሙጬ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW