1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
እምነትአፍሪቃ

1446ኛው የኢድ አል አደሀ በዓል

ዓለምነው መኮንን
ዓርብ፣ ግንቦት 29 2017

ሕዝበ ሙስሊሙ የዘንድሮውን 1446ኛው የኢድ አል አድሀ በዓል ሲያከበር የተፈናቀሉና ወላጆቻቸውን ያጡ ህፃናትን በመደገፍ ጭምር እንዲሆን የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጠየቀ ። በዓሉ ነገ በመላው የእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ይከበራል ።

1446ኛው የኢድ አል አደሀ በዓል
1446ኛው የኢድ አል አደሀ በዓል ምስል፦ Alemnew Mekonnen/DW

«ወላጆቻቸውን በሞት ያጡ ህፃናት ከወላጆቻቸው ጋር የዋሉ ያክል እንዲሰማቸው ያሻል»

This browser does not support the audio element.

ሕዝበ ሙስሊሙ የዘንድሮውን 1446ኛው የኢድ አል አድሀ በዓል ሲያከበር የተፈናቀሉና ወላጆቻቸውን ያጡ ህፃናትን በመደገፍ ጭምር እንዲሆን የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጠየቀ ።  በዓሉ ነገ በመላው የእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ይከበራል ። 

የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የዘንድሮውን 1446ኛው የኢድ አል አደሀ በዓል ምክንያት በማድረግ ትናንት በምክር ቤቱ ጽ/ቤት መግልጫ ስጥቷል ።

«በዓሉን በጋራ ማክበር ያስፈልጋል» ሼክ ጀህዋር መሐመድ

የምክር ቤቱ ፕረዚደንት ሼክ ጀህዋር መሐመድ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፣ ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር በጋራ፣ በመተባበር በተለይ ደግሞ የተፈናቀሉ ወገኖችን በማሰብና በማካፍል መሆን ይገባዋል፣ ፍቅር አንድነትና መተሳሰብ፣ መተዛዘን በተግባር የሚታይበት በዓል እንዲሆንም ሼክ ጀህዋር ጠይቀዋል፡፡

«ወላጆቻቸውን በሞት ያጡ ህፃናት ከወላጆቻቸው ጋር የዋሉ ያክል እንዲሰማቸው ያሻል»

የኢድ አል አደሀ በዓል እርድ በስፋት የሚካሄድበት በዓል መሆኑን የጠቀሱት ደግሞ የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የትምህርትና ዳዕዋ ዘርፍ ኃላፊ ሼክ መሐመድ ኢብራሒም ሲሆኑ ሐይማኖቱ በሚፈቅደው መሠረት  እርዱን ለምስኪኖች ማከፋፈል እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡ ወላጆቻቸውን በሞትና በሌሎች ምክንያቶች ያጡ ህፃናት በዓሉን ልክ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የዋሉ ያክል እንዲሰማቸው ማድረግ ተገቢ መሆኑንም ኃላፊው በመግለጫቸው አመልክተዋል ።

የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አመራርምስል፦ Alemnew Mekonnen/DW

"ተተኪው ትውልድ መስጠትን ከእኛ ወላጆች ማየትና ልምድ ማድረግና በተግባር ማሳየት አለበት” ሲሉ ሼክ መሐመድ ተናግረዋል፡፡

«ለሠላም መፀለይ ያስፍልጋል» አባ ገዳ አህመድ መሐመድ

በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር አባ ገዳ አህመድ መሐመድ በበኩላቸው፣ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ሐይማኖቱ በሚፈቅደው መሠረት በዓሉን ማክበር እንደሚገባ ጠቁመው በአጠቃላይ በአገራችንና በተለይ በአማራ ክልል ሠላም ሰፍኖ ሁሉም በሠላም ወጥቶ የሚገባበት ጊዜ እንዲመጣ ፈጣሪን በፀሎት መጠየቅ እንደሚገባ ለዶይቼ ቬሌ ከከሚሴ ከተማ በስልክ ተናግረዋል፡፡

1446ኛው የኢድ አል አደሀ በዓል በእምነቱ ተካታዮች ዘንድ በመላው ዓለም ነገ ይከበራል፡ ፡

ዓለምነው መኮንን

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሠ

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW