1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

16ኛው ታላቁ ሩጫ

እሑድ፣ ኅዳር 11 2009

42 000 ሰዎች የተሳተፉበት 16ኛው ታላቁ ሩጫ ዛሬ በአዲስ አበባ ተካሔደ። የኢትዮጵያ መንግሥት ገቢራዊ ካደረገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በኋላ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ የተሳተፈበት የአደባባይ ውድድር በሰላም መጠናቀቁን የዶይቼ ቬለ ወኪል ዮሐንስ ገብረ እግዚዓብሔር ከአዲስ አበባ ዘግቧል።

Äthiopien Marathon Addis Abeba Straßenlauf
ምስል DW/Y.G. Egziabher

Great Ethiopian Run Addis - MP3-Stereo

This browser does not support the audio element.

 በውድድሩም ከተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች እና ከመዲናዋ የተውጣጡ ኢትዮጵያውያን እና የውጭ ሀገር ዜጎች ተካፍለዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ገቢራዊ ካደረገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በኋላ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ የተሳተፈበት የአደባባይ ውድድር በሰላም መጠናቀቁን የዶይቼ ቬለ ወኪል ዮሐንስ ገብረ እግዚዓብሔር ከአዲስ አበባ ዘግቧል። በአትሌቶች ምድብ የተካሔደውን ውድድር በወንዶች አትሌት አቤ ጋሻሁን ከአማራ ማረሚያ ቤት አንደኛ፤ኬንያዊው ጆሩም ሉምባሲ ሁለተኛ እንዲሁም የኦሮሚያ ፖሊሱ አዱኛ ታከለ  ሶስተኛ ሆነው አጠናቀዋል። በሴቶች ጎራ ፎቴን ተስፋዬ ከመሰቦ ስፖርት ክለብ አንደኛ፤ሙልዬ ደቀቦ ከኦሮሚያ ፖሊስ ሁለተኛ እንዲሁም ታደለች በዳሶ ከኦሮሚያ ማረሚያ ቤት ሶስተኛ በመውጣት አጠናቀዋል። የታላቅ ሩጫ አዘጋጅ እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ አዲስ አበባ ለአትሌቶች አትመችም ያልኩትን ሀሳብ የዛሬው ሩጫ አስመስክሮልኛል ይላል።  ለዚህም ምክንያቱ አሸናፊዎች ከክልል የመጡ ተወዳዳሪዎች በመሆናቸው ነው። 

ዝርዝር ዘገባውን በድምፅ ያገኙታል።

 


ዮሐንስ ገብረ እግዚዓብሔር

ልደት አበበ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW