1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

17 ኛዉ የብሪክስ ጉባኤ - ትራምፕ የብሪክስ ጥምረትን ለምን ፈሩት?

ገበያው ንጉሤ
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 1 2017

ሪዮ ዲ ጄኒሮ ብራዚል ለሁለት ቀናት ለጉባኤ የተቀመጠዉ የብሪክስ ስብስብ ለትራምፕ የኤኮኖሚ ፖሊሲ ምላሽ በመስጠት ተጠናቋል። ጥምረቱ እንደ ቻይና ያሉ አገራትን ቢያካትትም እስካሁን እምብዛም ስኬት አላመጣም። በ17ኛዉ የብሪክስ ጉባኤ የቻይናና የሩሲያ መሪዎች በአካል አልተገኙም፤ የኢራንና ግብጽ መሪዎች ደሞ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው ተወክለዋል።

17 ኛዉ የብሪክስ ጉባኤ
17 ኛዉ የብሪክስ ጉባኤምስል፦ Eraldo Peres/AP Photo/picture alliance

17 ኛዉ የብሪክስ ጉባኤ - ትራምፕ የብሪክስ ጥምረትን ለምን ፈሩት ?

This browser does not support the audio element.

 

የብሪክስ አባል ሃገራት ጥምረት በኤኬኖሚ የበለጸጉ የቡድን ሰባት አባል ሃገራትን ለመገዳደር  በብራዚል፤ ሩስያ ፣ ህንድ ፣ ቻይና ፣ እና ደቡብ አፍሪቃ በጥምረት የመሰረተዉ በኋላ ላይ  ኢትዮጵያ ፣ ግብጽ ፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ፣ የተቀላቀሉበት የብሪክስ ስብስብ የአሜሪካኑን ፕሬዚዳንት ትራምፕን እንዳስፈራ እየተዘገበ ነዉ። ሪዮ ዲ ጄኒሮ ብራዚል ለሁለት ቀናት ጉባኤ ተቀምጦ ትናንት ሰኞ የተጠናቀቀዉ ጉባኤ ለትራምፕ ጠንካራ የኤኮኖሚ ፖሊሲ ምላሽ ይሰጣል ተብሎም  ነበር። ጥምረቱ እንደ ቻይና ያሉ በኤኮኖሞ የበለፀጉ አገራትን ቢያካትትም እስካሁን እምብዛም ስኬት አላስመዘገበም። ብዙ አገራት የብሪክስ ጥምረት  አባል ለመሆን እንደሚፈልጉ ተመልክቷል።

አስራ 17 ኛው የብሪክስ ጉባኤ በሪዮ - ብራዚል


ባለፈው ቅዳሜ በብራዚል ሪዮ ዴ ጃኔሮ  የተጀመረው በማደግ ላይ ያሉ አገሮች ስብሰብ (ብሪክስ) 17ኛ ጉባኤ ሰኞ የጋራ መገልጫዎችን በማውጣትና ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል። ብራዚል፤ ሩሲያ፤ ህንድ፤ ቻይናና ደቡብ አፍርቃ በምዕራባዊው የኢኮኖሚና ፖለቲካ ተጽኖ አንጻር  እንደ ጎርጎረሳዉያኑ በ2009 ዓ.ም የመሰረተዉ ስብሰብ፤ ዛሬ ኤትዮጵያንና ግብጽን ጨምሮ አስራ አንድ የእስያና የአረብ አገሮችን ያካተተ ሲሆን፤ ሌሎች በርካታ አገሮችም ሊቀላቀሉት ጥያቄ እያቀረቡ መሆኑ ታውቋል። በጉባኤው ከነባሮቹ አገሮች የቻይና እና የሩሲያ መሪዎች በአካል አልተገኙም፤ የኢራንና ግብጽ መሪዎችም የተወከሉት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው ነው።  16ኛው የብሪክስ ጉባኤ በሩሲያ - ካዛን


ጉባኤው የተጠራበት ልዩ ወቅት
 ጉባኤው የተጠራውና የተከሄደው የስብስቡ አባል በሆነቸው ኢራን ላይ አሚሪካ የሚሳይል ጥቃት በፈጸመችበት ማግስትና ፕሬዝዳንት ትራምፕ በስብስቡ አባል አገሮችና በአውሮፓ ጭምር የንግድ ጦርነት በክፈቱበት ወቅት መሆኑ የብዙዎችን ትኩርት ስቧል።
የጉባኤው አስተናጋጅ አገር መሪ ፕሬዝዳንት ልዊዝ ኢናሲዮ ሉላ በጉባኤ መክፈቻ ንግግራቸው ፋሺሽዝም ከተሸነፈና የመንግስታቱ ድርጅት ከተመሰረተ ሰሚኒያ ዓመታት በሁዋላ የድርጅቱን መዳከምና የባለብዙ ወገን ፖለቲካ መቅረትን በዓይናችን እያየን ነው፤ በማለት የመግንስታቱ ድርጅት ዛሬ አለ ሊባል እንደማይቻል አስታውቀዋል ። በአየር ንብረት ለውጥና የንግድ ስርአት ላይ የተገኙ ድሎች የተቀለበሱና ይልቁንም በዓለማችን ወታደራዊ ግምባታ እያደገና የጦርነት ስጋትም እያየለ መምጣቱን በመጥቀስም ብሪክስ ይህን የአለማችንን አደገኛ አካሄድ ለመግታት የራሱን ጥረት እንደሚያደርግ አስግንዝበዋል።ብሪክስ ጉባኤ፦ በአፍሪቃ እንዴት ይታያል?

ፕሬዚዳንት ትራምፕ የብሪክስ አባል አገራትን በቀረጥ ጭማሪ ማስፈራራታቸዉን ተከትሎ ሞስኮ የሚገኝ ሰዓሊ የሳለዉ ምስል ነዉ ። ስዕሉ ላይ ባለዉ ምስል ላይ የተፃፈዉ በሩስያ ቋንቋ ብሪክስ ይላል። ምስል፦ DW


የጉባኤው መግለጫና የፕሬዝዳንት ትራም ማስፈራሪያ

የጉባኤው ተሳታፊዎች በጋራ ባወጡት ባለ 31 ገጽ የጋራ መግለጫ በኢራን ላይ የተጸመውን ወታደራዊ ጥቃትና በጋዛ እየተካሄደ ያለውን ዘመቻ እንዲሁም የዓለምን ንግድ እያወከ ያለውን በሸቀጦች ላይ የተጣለውን ተጨማሪ  ታክስ አውግዝዋል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በበኩላቸው በማህበራዊ ገጻቸው፤ ጸረ አሜሪካ ከሚሉት ብሪክስ ጋር ባበሩና በወገኑ አገሮች ላይ የ10 %  ተጨማሪ ታክስ የሚጥሉ መሆኑን አስታውቀዋል።
ለፕሬዝዳንቱ ማስጠንቀቂያ ካአባል አገሮች የተሰጠ መልስ

 ከስብስቡ ውስጥ ቻይና ሩሲያና ደቡብ አፍርቃ ስብስቡ ጸረ አሜሪካ አቋም እንደሌለውና  ግጭት ውስጥም መግባት እንደማይፈልግ ገልጸው ፕሬዝዳንቱ ለሰነዘሩት የማስፈራሪያ መገግለጫ ተቃውሟቸውን በዲፖላሲያዊ ቋንቋ  አሳውቀዋል። የስብሰባው መሪ ፕሬዛንት ሉላ ግን ከዚህ በተለይና ከረረ ባለ ቋንቋ ‘እኛ ንጉሰ ነገስት የማያስፈልገን ለኡላዊ አገሮች ነን’ በማለት የፕሬዝዳንት ትራምፕን ማስፈራርያና ዛቻ አጣጥለውታል።የኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነት አንድምታ

የብሪክስ አባል ሃገራት መስፋፋት 


አጠቃላይ የጉባኤው መግለጫ ይዘት
በአጠቃላይ ግን የጉባኤው መግለጫ አሜርካንንም ሆነ ፕሬዝዳንት ትራምፕን በቀጥታ የሚጠቅስ እንዳይሆን ተደርጎ በጥንቃቄ እንደተዘጋጀ ነው የሚነገረው። ያም ሆኖ በተለይ የአየር ንብረትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መዋቅር ለውጥ ጉዳዮች በመግለጫው በሰፊውና በጥልቀት ተነስተዋል። የደቡብ አፍርካው መሪ ሲሪል ራማፉዛ  ከጉባኤው የወጣውን የጋራ መመገለጫ ሲያብራሩ፤ “ በመግለጫው  በርካታ ጉዳዮች ተካታዋል። የመንግስታቱ ድርጅት መዋቅር መሻሻል ያለበት መሆኑ ተጠቅሷል፤ ተጠይቋልም። በተለይ 1.3 ቢሊዮን ህዝብ ያለው አፍርካ በጸጥታው ምክር ቤት  ድምጽ አልባ መሆኑ ተቀባነት የለውም” በማለት የአየር ንብረት አጀንዳም በጉባኤው ትኩረት  የተሰጠው ኧንደነበር አስረድተዋል ። ፕሬዝዳንት ራማፉዛ  አክለውም “ ሁላችንም በጋራ በኢራን የተፈጽመውን ወታደራዊ ጥቃት አውግዘን፤ ባጋዛ የተኩስ ማቆም እንዲደረግና በፍልጽስጤሞች ላይ የሚፈጸመው የዘር ማጥፋት እርምጃ እንዲቆም ጠይቀናል” ብለዋል።


የብሪክስና አባሎቹ ተግዳሮቶች
ይሁን እንጂ በብሪክስ የተለያየ ፍላጎት ያላቸው እንደ ኢራንና ሩሲያ የመሰሉ ከአሜሪካ ጋር ቅራኔ ውስጥ የገቡና፤ እንደ ህንድ፤ ብራዚልና ሌሎች ከአሜሪካ ጋር ግንኑነታቸውን ማጠናከር የሚፈልጉ አገሮች የሚገኙበት መሆኑ የድርጅቱን አንድነት ቀጣይነት አስቸጋሪ እንደሚያደርገው እየተነገረ ነው። በተለይ እንደ ሳኡዲ አረቢያና ሌሎች ከአሜሪካ ጋር የጠበቀ ግንኑነት ያላቸው አገሮች በብሪክስ አባልነታቸውና  ተሳትፎአቸው አሜሪካ በተለይም ፕሬዝዳንት ትራም ፊታቸውን እንዳይዞሩባቸው የሚሰጉ ስለመሆኑ በሰፊው መነገር ይዟል ።


ገበያው ንጉሴ
አዜብ ታደሰ 
እሸቴ በቀለ
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ
ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW