19ኛዉ የኢትዮጵያ ጥናት ጉባዔ በዋርሶ
ሐሙስ፣ መስከረም 13 2008ማስታወቂያ
ፖላንድ ዋርሶ ላይ ስለተካሄደዉ ስለ 19ኛዉ የኢትዮጵያ ጥናት ዓለም አቀፍ ጉባዔ የነገሩን የኢትዮጵያ የጥናትና ምርምር ተቋም ዳይሬክተር ዶክተር አህመድ ሀሰን ነበሩ ጤናይስጥልኝ አድማጮች እደምን አመሻችሁ። የጥንታዊ ቅርሶችና ታሪክ ባለቤት የሆነችዉ ኢትዮጵያ ከረጅም ጊዜ አንስቶ የታሪክ የቅርስ ተመራማሪዎችን ትኩረት እንደሳበች ናት። ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚካሄዱት የተለያዩ ጥናቶች ግብዓትነት ትልቅ አስተዋፅኦን ማድረጉም ይታወቃል። ለዚህም ከ60 ዓመት በላይ የሆነዉ የኢትዮጵያ ጥናት ዓለም አቀፍ ጉባዔ ተጠቃሽ ነዉ። ስለጉባኤዉ ፋይዳ ኢትዮጵያዉያንና ጀርመናዊ ተሳታፊን አነጋግረንናል።