2014 ወደኋላ ሲቃኝ
እሑድ፣ ታኅሣሥ 19 2007ማስታወቂያ
ዓመቱ መላዉን ዓለም የነኩና በተለያዩ አካባቢዎችና አሕጉሮችም ያተኮሩ ተግባራት አስተናግዷል። የደቡብ ሱዳን ፖለቲከኞች የገጠሙት ዉጊያ ተጠናክሮ ድርድር ሽምግልናዉ ሳይሳካ የበርካቶችን ሕይወት ቀጥፎ በሚሊዮን የሚገመቱትን ለስደት የዳረገዉ በዚሁ ዓመት ነዉ። የዩክሬን የፖለቲካ ዉዝግብ ተባብሶ ኃያላኑን በሁለት ጎራ ከፍሎ ወደቀዝቃዛዉ ጦርነት ሊመልስ የዳዳዉም በ2014 ነዉ። አሜሪካን ዉስጥ የነጭ ጥቁር የቀለም ልዩነት መዳፈን እንጂ እንዳልጠፋም በዚሁ ዓመት ታይቷል። በአዉሮጳ ደግሞ ቀኝ አክራሪዎች አንሰራርተዉ ታይተዋል። የዶቼ ቬለ የዚህ ሳምንት የእንወያይ ርዕስ ነዉ። ከድምፅ ዘገባዉ ያድምጡ።
ሸዋዬ ለገሠ