1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

21ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ

እሑድ፣ ጥር 15 2014

ዛሬ ለ21ኛ ጊዜ አዲስ አበባ መስቀል አደባባይን መነሻ እና መድረሻው አድርጎ የተካሄደው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሴቶች አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው እንዲሁም በወንዶች አትሌት ገመቹ ዲዳን አሸናፊ አድርጎ ተጠናቋል።

Äthiopien | Great Run 2022
ምስል Seyoum Getu/DW

This browser does not support the audio element.

 ህብረት አንድነትን ያጠናክራል የሚባልለት፤ በአህጉሪቱ ትልቁ የጎዳና ላይ የአትሌቲክስ ፌስቲቫልም እንደሆነ የሚነገርለት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዛሬ ለ21ኛ ጊዜ ነው በመዲናዋ በደማቅ ሥነ-ስርዓት ተካሂዶ የዋለው፡፡ በስፖርታዊ ውድድሩ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን አትሌቶችና ከጎረቤት አገሮች የመጡ አትሌቶች እንዲሁም የሩጫ ፌስቲቫሉ ተሳታፊዎች ተገኝተው አድምቀውታል።
በተካሄደው የአትሌቶች ሩጫ በሴቶች አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው 1ኛ ስትወጣ ግርማዊት ገ/እግዚአብሔር 2ኛ እንዲሁም መልክናት ውዱ በ3ኛ ውድድሩን አጠናቀዋል። 
በወንዶች ደግሞ አትሌት ገመቹ ዲዳ ነው 21ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያን በአንደኝነት የደመደመው፡፡ አትሌት ጌታነህ ሞላ እና አትሌት ቦኪ ድሪባ በ2ኛ እና 3ኛ ደረጃ ተከትለውታል። ከባድ የአየር ሁኔታ ከብርቱ አትሌቶች ጋር መፋለምን ፈታኝ እንዳረገበት  አትሌት ገመቹ  ለዶይቼ ቬለ ገልጿል።
ህዳር 5 ቀን 2014 ዓ.ም ሊካሄድ የነበረውን የ2014 ቶታል ኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ፥ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሰረት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሞ ነው ዛሬ የተካሄደው። በውድድሩ በርካታ የውጭ አገራት ዜጎችም ተሳታፊ ነበሩ፡፡ 
በውድድሩ ላይ የሚሳተፉ ሌሎች ታዳሚንም ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ህብረትና አንድነትን በማስረጽ ረገድ ከስፖርታዊነቱ ሌላ የሚኖረው አስተዋጽኦ ነው ሲሉ ይገልጹታል፡፡
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በዓለም በ6ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ትልቁ የጎዳና ላይ ሩጫ ሲሆን፤ በአፍሪቃ ደግሞ በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡ 
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ የተካሄደው 21ኛውን የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በማስመልከት ባስተላለፉት መልእክትም ዝግጅቱ አንድነትን በመፍጠር ጉልህ ሚና ያለው ብለውታል።
የዛሬው ውድድሩ በሠላም መጠናቀቁንም የአዲስ አበባ ፖሊስ ከሁኔቱ መጠናቀቅ በኋላ ባስተላለፈው መልእክት አስታውቋል፡፡

ምስል Seyoum Getu/DW
ምስል Seyoum Getu/DW

ስዩም ጌቱ

ልደት አበበ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW