1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

27ኛዉ የአፋር ጉባዔ በብራስልስ

ዓርብ፣ ሐምሌ 20 2010

የአፋር መድረክ ጉባዔ ከትናንት ጀምሮ ለሦስት ቀናት እየተካሄደ ነዉ። በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የተጀመረዉ የወዳጅነት ግንኙነት ዘላቂነት እንዲኖረዉም የአፋርን ማኅበረሰብ ማሳተፍ እንዳለበት የሚያሳስቡ ጥያቂዎችን አንስተዋል።

Belgien Wenig Touristen auf dem Grand Place in Brüssel
ምስል Getty Images/AFP/T. Monasse

የለዉጥ እንቅስቃሴ አፋር ክልል አልደረሰም

This browser does not support the audio element.

የአፋር መድረክ ጉባዔ ከትናንት ጀምሮ ለሦስት ቀናት እየተካሄደ ነዉ። የአፍር መድረክ በአፍሪቃ ቀንድ የሚኖሩ የአፍር ማኅበረሰቦች በጋራና በየግል የሚደርስባቸዉን የፖለቲካና ማኅበራዊ ችግሮች በጥልቀት የሚመረምሩ ስብሰባዎችንን እና ጉባዔዎችን የሚያካሂዱ  ሲሆን ይህ የዘንድሮ ስብሰባ 27 ኛዉ መሆኑ ታዉቋል። በስብሰባዉ ከሰሜን አሜሪካ ከአዉሮጳ የተለያዩ ሃገሮች እና ከኢትዮጵያ ጭምር የመጡ የአፍር የፖለቲካና የወጣቶች ሴቶችና የሰብዓዊ መብቶች እንዲሁም የአደረጃጀት ተወካዮች ተገኝተዋል። በቤልጄየም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለመጀመርያ ጊዜ ተጋብዞ አቶ ገብረሚካኤል ገብረ ጻድቅ የኤምባሲዉ ምክትል ኃላፊ በመክፈቻዉ ሥነ-ስርዓት ላይ ተገኝተዉ ንግግር አድርገዋል። አቶ ገብረፃድቅ ባደረጉት ንግግር ዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ የተደረጉትን ለዉጦችና የተገኙትን ዉጤቶች ጠቅሰዉ ኤምባሲዉ ከአፋርም ሆነ ከሌሎች ስብስቦች ጋር አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አስታዉቀዋል። ተሰብሳቢዎቹ በሃገር ደረጃ እየተደረገ ያለዉን የለዉጥ እንቅስቃሴ እንደሚደግፉ በመግለፅ ለዉጡ ግን ወደ አፋር ክልል እንዳልደረሰ ተናግረዋል። በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የተጀመረዉ የወዳጅነት ግንኙነት ዘላቂነት እንዲኖረዉም የአፋርን ማኅበረሰብ ማሳተፍ እንዳለበት የሚያሳስቡ ጥያቂዎችን አንስተዋል። አምባሳደሩም ጥያቄዎቹን ለማዕከላዊዉ መንግሥት የሚያሳልፉ መሆኑን አሳዉቀዋል።  

ገበያዉ ንጉሤ

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW