5 የፖለቲካ ድርጅቶች በፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ላይ ያነሱት ቅሬታ
ዓርብ፣ መስከረም 24 2017ከ60 በላይ የፖለቲካ ድርጅቶችን ያቀፈው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የአመራር ዘመኑ ነሐሴ 13 ቀን 2016 ዓ.ም ተጠናቆ እያለ "በመተዳደሪያ ደንቡ የተጣለበትን ተግባርና ኃላፊነት በአግባቡ ሊወጣ አልቻለም የሚል ቅሬታ ቢቀርብበትም ለማድመጥና ለማሻሻል አልቻለም" ሲሉ አቤቱታ ያቀረቡበት ኢሕአፓ፣ ኦነግ፣ ሕብር ኢትዮጵያ፣ ኦፌኮ እና የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ ናቸው። አቶ አማኑኤል ሞጊሶ የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ (ዎብን) ሊቀመንበር።"የጋራ ምክር ቤቱ አባላት የማያውቁትን የማሻሻያ ጥያቄ ለምርጫ ቦርድ ማስገባቱ ግልጽ ሄኗል »ብለዋል።የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጥሪ
አቤቱታው የቀረበበትሰብሳቢ አቶ ደስታ ዲንቃ ፓርቲዎቹ ይህንን ቅሬታ ለማቅረብ "ለምን እንደቸኮሉ አናውቅም፣ ለእኛም ይህንን አላሳወቁንም" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
ጠቅላላ ጉባኤ ለማድረግም ድጋፍ የሚያደርግ አካል እያፈላለግን በጥረት ላይ ነበርን የሚሉት ሰብሳቢው፣ የጋራ ምክር ቤቱ በእሥር ላይ የነበሩ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን ለማስፈታት ጥረት ሲያደርግ እንደነበር፣ በመንግሥት እና በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል ጥረት ውስጥ መቆየታቸውን በመጥቀስ ጠቅላላ ጉባኤ አድርገው የአመራር ለውጥ ለማድረግ የዘገዩት በዚህ ምክንያት መሆኑን ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል።
ተቃውሞ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት መግለጫ ላይ
አምስቱ ፓርቲዎቹ ግን ምርጫ ቦርድ ይህንን ሕገ ወጥ ወጥ እና ከፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አሰራር ውጭ ያሉትና በፓርቲዎች መካከል ያለው የጋራ ጉዳይ በመተማመን መንፈስ የማስፈፀም ፍላጎት የሚጎዳ ያሉትን ተግባርና አካሄድ ጣልቃ በመግባት ማስቆም አለበት ብለዋል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ