1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

7ኛው ዙር የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ዘመቻ በኢትዮጵያ

ሰኞ፣ ኅዳር 9 2017

የዚሁ ትምህርት ቤት ተማሪ አርሴማ ጓደኞቿ እድሉን እንዲጠቀሙበት መልዕክት አስተላልፋለች፡፡ ክትባቱ የጎላ የህመም ስሜት እንደሌለው ያመለከተችው አርሴማ የትምህርት ቤት ጓደኞቿም ሆኑ የሰፈር አብሮአደጎቿ እንዲከተቡ አደራ ብላለች፡፡የአማራ ክልል ሐይማኖት ተቋማት ምክር ቤት ህብረተስቡ ህፃናት ክትባቱን እንዲወስዱ እንዲያደርግ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

7ኛው ዙር የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ዘመቻ በኢትዮጵያ
7ኛው ዙር የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ዘመቻ በኢትዮጵያምስል Alemnew Mekonnen/DW

7ኛው ዙር የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ዘመቻ

This browser does not support the audio element.

ክትባቱ ዛሬ በባሕርዳር ከተማ ድልችቦ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲጅመር የተገኙት በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሚኒስትሯ የክትባት አማካሪ አቶ ዮሐንስ ላቀው እንዳሉት በዚህ 7ኛ ዙር በተባለው የክትባት ዘመቻ 7 ሚሊዮን 500 ሺህ እድሜያቸው ክ9 እስክ 14 ዓመት የሆነ ታዲጊ ሴት ህፃናት ክትባቱን ይወስዳሉ፡፡

በአማራ ክልል 1.6 ሚሊዮን ህፃናት የማህፀን በር ክትባት ይወስዳሉ

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ የእናቶችና ህፃናት ክትትል ዳይሬክተር አቶ መልሰው ጫንያለው በበበኩላቸው በአማራ ክልል 1 ሚሊዮን 600 ሺህ ወጣት ሴቶች ክትባቱን ያገኛሉ ብለዋል፡፡ እንደኃላፊው ከ2011 ዓም ጅመሮ ለ7ኛ ጊዜ የሚስጠው ክትባት ከ9 ዓመት እስከ 14 ዓመት ክልል የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ወጣተ ሴቶች ናቸው፡፡ በዚህ ዓመት ክትባቱን የሚወስዱ ሴቶች ቁጠር ከፍተኛ መሆኑን አመልክተው፣ ይህም በአማራ ክልል ብቻ ተካታቢዎች 1.6 ሚሊዮን ናቸው ብለዋል፡፡ ይህ ቁጥር ባለፉት 6 ዓመታት የተከተቡትን እንደሚስተካከልም አቶ መልሰው ተናግረዋል፡፡በባሕርዳር ከተማ ድል ችቦ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ክትባቱን ካገኙ ተማሪዎች መካክል ተማሪ ዳናዊት ደረጀን ስለክትባቱ አስፈላጊነት ተናግራለች፡፡የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት በኢትዮጵያ

አስቀድሞ መጠንቀቅ ያስፈልጋል አስፈላጊነት

“መጀመሪያ ጥንቃቄ አስፈላጊ ነው፣ ከዚያ ባለፈ ደግሞ የመጣውን እድል መጠቀም ጊዜ ሊስጠው አይገባም” ብላለች፡፡ አርሴማ ጥላሁን የተባለች ሌላ የዚሁ ትምህርት ቤት ተማሪም ጓደኞቿ እድሉን እንዲጠቀሙበት መልዕክት አስተላልፋለች፡፡ ክትባቱ የጎላ የህመም ስሜት እንደሌለው ያመለከተችው አርሴማ የትምህርት ቤት ጓደኞቿም ሆኑ የሰፈር አብሮአደጎቿ እንዲከተቡ አደራ ብላለች፡፡

7ኛው ዙር የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ዘመቻ በኢትዮጵያምስል Alemnew Mekonnen/DW

ኅብረተሰቡ ክትባትን ሊለምደው ይገባል

የአማራ ክልል ሐይማኖት ተቋማት ምክር ቤት አስተባባሪ አቶ ፋሲል ታዬ ህብረተስቡ ህፃናት ክትባቱን እንዲወስዱ በማድረግ ከሞት እንዲታደጋቸው ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ባልዳበረበት ጊዜ በሽታዎች ህብረተስቡን በከፍተኛ ሁኔታ ይጎዱ እንደነበር አመልክተዋል፡፡በመሆኑም ወላጆች ህፃናቱ እንዲከተቡ ማድረግ ተገቢ መሆኑን አቶ ፋሲል ገልጠዋል፡፡ ህብረተሰቡም ክትባትን ልምዱ ሊያደርገው እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡

 መጠናከር የሚሻ የህክምና ዘርፍ

የማህፀን በር ካንሰር በኢትዮጵያ በየዓመቱ የ8000 እናቶችንና ወጣት ሴቶችን ህይወተ እንደሚቀጥፍ የጤና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ 5 ቀናት በመላ አገሪቱ እንደሚሰጥ የጤና ባለሙያዎቹ ገልጠዋል፡፡

ዓለምነው መኮንን
ኂሩት መለሰ
ታምራት ዲንሳ 
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW