1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በካን ፊልም ፌስቲቫል ኢትዮጵያ ራሷን አስታዋውቃለች

ሐሙስ፣ ግንቦት 15 2011

በዘንድሮው የካን ፊልም ፌስቲቫል ኢትዮጵያን ጨምሮ 15 የአፍሪካ ሀገራት ተካፋይ የሆኑበት "የአፍሪካ መንደር" የተሰኘ ፓቭሊዮን የፊልም ባለሙያዎችን አስተናግዷል። ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፍ የፊልም ቀረጻ ስራዎች አመቺ የተፈጥሮ አቀማመጥ ያላት መሆኗን ለፊልም ሰሪ ኩባንያዎች ያስተዋወቀችበት መድረክም ካን ላይ ተካሂዷል።

Cannes Filmfestival 2019 | Afrikanischer Pavillion
ምስል DW/H. Tiruneh

በካን ፊልም ፌስቲቫል ኢትዮጵያ ራሷን አስታዋውቃለች

This browser does not support the audio element.

በደቡብ ምስራቃዊ የፈረንሳይ ክፍል በሚገኘው የፍሬንች ሪቬሪያ የሚዴትራንያንን የባህር ዳርቻ ተንተርሳ የምትገኘው ውቧ የካን ከተማ ሰሞኑን በዓለማችን ዕውቅ የፊልም ተዋንያን፣ አዘጋጆች፣ ሞዴሎች እና ሌሎች ስመ ጥር ግለሰቦች ተጥለቅልቃ ነው የሰነበተችው።

እነዚህ እንግዶች ወደ ከተማይቱ ብቅ ያሉት በዓለም አቀፉ የካን ፊልም ፌስቲቫል ላይ ለመታደም ነው። በርካታ መገናኛ ብዙሃንም አይኖቻቸውን ላይ አድርገው ከርመዋል። የከተማዋ ነዋሪዎች እና ለእዚሁ ፌስቲቫል ወደ ካን የመጡ አገር ጎብኚዎችም እንደ ጥምቀት በዓል ባማረ እና በተሽቀረቀረ አለባበስ በየጎዳናዎቿ ልዩ ድምቀት ሆነው ታይተዋል።

ምስል DW/H. Tiruneh

ዘንድሮ 72ኛ ዓመቱን ያስቆጠረው የካን ፊልም ፌስቲቫል እንደጎርጎሮሳዊው 1946 ዓ. ም. ነበር መሰረቱን የጣለው። በዚሁ የፌልም ፌስቲቫል ላይ በፊልም ኢንዱስትሪው ገዢ እና ሻጭን፣ አከፋፋይ እና ፊልም ሰሪዎችን የሚያገናኘው የፌስቲቫሉ አካል የሆነው የፊልም ገበያ ወይም ማርሼ ዱፌል በመባል የሚታወቀው ነው።

የዘንድሮው የካን ፌስቲቫል ለአፍሪካ የፊልም ኢንዱስትሪ አዲስ ምዕራፍ የተከፈተበት ሆኗል። የአፍሪካ የፊልም ባለሙያዎችም ባገናኘው "የአፍሪካ መንደር" (ፓቭሊዮን አፍሪክ) ኢትዮጵያን ጨምሮ 15 የአፍሪካ ሀገራት ተካፋይ ሆነውበታል። ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፍ የፊልም ቀረጻ ስራዎች አመቺ የተፈጥሮ አቀማመጥ ያላት መሆኗን ለዓለም አቀፍ ፊልም ሰሪ ኩባንያዎች ያስተዋወቀችበት መድረክም ካን ላይ ተካሂዷል።

ሃይማኖት ጥሩነህ 

ተስፋለም ወልደየስ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW