73 ተኛው የድል በዓል
ሰኞ፣ ሚያዝያ 27 2006ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ በፋሺሽት ኢጣልያ ላይ ድል የተቀዳጀችበት 73 ተኛ ዓመት በዓል በመላው ኢትዮጵያ ዛሬ ተከብሮ ዋለ ። በዓሉ በተለይም በአዲስ አበባ በተለምዶ አራት ኪሎ ተብሎ በሚጠራው የድል አደባባባይ በሚገኝበት ስፍራ በድምቀት ተከብሯል ። የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ አርበኞችና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት በተካሄደው የበዓሉ አከባበር ስነ ስርዓት ላይ ለሃገራቸው የተዋደቁ አርበኞች የሚያገኙት የጡረታ ገንዘብ እንዲሻሻል ተጠይቋል ። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ተክሌ የኋላ
ሂሩት መለሰ