1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

82 ኛዉ የኢትዮጵያዉያን የድል በዓል በድምቀት ተከበረ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 27 2015

ኢትዮጵያ ከጣሊያን ዳግማዊ ወረራ ተላቃ በ1933 ዓ.ም. ከአደዋ ድል በኋላም ዳግም ነጻነቷን ያረጋገጠችበት እለት የሚታወስበት የአርበኞች ቀን ዛሬ አዲስ አበባ በአርበኞች ሃውልት እለቱ ለ82ኛ ጊዜ ነው ታውሶ የዋለው፡፡ ዕለቱን በማስመልከት ማለዳ ላይ መድፍ ተተኩሷል፡፡ የአገሪቱ ርዕሰ ብሔር አርበኞች አደባባይ ተገኝተው የአበባ ጉንጉን አኑረዋል፡፡

Äthiopien Addis Abeba | Feier des äthiopischen Patriots Day
ምስል፦ Seyoum Getu/DW

«ኢትዮጵያዉያን ቅኝ ገዢዎች ተደላድለው የሚኖሩባት አገር አለመሆኗያረጋገጡበት እለት ነው»

This browser does not support the audio element.

ኢትዮጵያ ከጣሊያን ዳግማዊ ወረራ ተላቃ በ1933 ዓ.ም. ከአደዋ ድል በኋላም ዳግም ነጻነቷን ያረጋገጠችበት እለት የሚታወስበት የአርበኞች ቀን ዛሬ አዲስ አበባ በአርበኞች ሃውልት እለቱ ለ82ኛ ጊዜ ነው ታውሶ የዋለው፡፡ ዕለቱን በማስመልከት ዛሬ ማለዳውን መድፍ ተተኩሷል፡፡ የአገሪቱ ርዕሰ ብሔርም በአርበኞች አደባባይ ተገኝተው በሃውልቱ ስር የአበባ ጉንጉን አኑረዋል፡፡ የጥንታዊ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳኒኤል ጆቴ እና የአገር መከላከያ ተወካዮችን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማትም በበዓል አከባበር ስርዓቱ ታድመው እለቱን አስታውሰዋል፡፡

82 ኛዉ የኢትዮጵያዉያን የድል በዓል ተከበረምስል፦ Seyoum Getu/DW

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እንደ ርዕሰ ብሔርነታቸው በስፍራው ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክትም፤ የዛሬው እለት አርበኞች ኢትዮጵያ ቅኝ ገዢዎች ጨርሶ ተደላድለው የሚኖሩባት አገር አለመሆኗን ለመጨረሻ ጊዜ ያረጋገጡበት ነው ብለዋል፡፡ “የአገር ፍቅር እና ክብርን የሰነቁ አርበኞች፤ የወራሪ ኃይልን ውድቀት ባፋጠኑበት ዛሬ በምናስታውሰው እለት፤ አገራችን ቅን ገዢዎች ተደላድለው ሊቀመጡባት የሚችሉበት አገር እንደማትሆን ለመጨረሻ ጊዜ ያረጋገጡበት ነው፡፡ ይህን ታሪክ መረዳት ያለንበትን ለማወቅ እና የወደፊቱንም ለማዘጋጀት ይረዳል፡፡”

ከ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ኢትዮጵያ የታላላቅ አገራት መዳረሻ ፍላጎት እንደነበረች አስታውሰው፤ ዛሬ የሚከበረው የአርበኞች ቀን ዋናው ግቡ በወቅቱ ጠላቶች የነበሩ አገራት ላይ ቁርሾ ለመያዝ አለመሆኑን ያወሱት ደግሞ የጥንታዊ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳኒኤል ጆቴ ናቸው፡፡ “እንደ ዛሬ ያሉትን የድል በዓላቶችን የምናከብረው ዛሬ ወዳጆች የሆኑንን እንደ ጣሊያን እና ሌሎች የአውሮፓ አገራት ላይም ቁርሾ ለመያዝ አይደለም፡፡ ትውልዱ የአባቶቹን ጀግንነት በመረከብ ኢትዮጵያን በሁለንተናው የማላቅ ኃላፊነቱን እንደዲወጣ ለማሳሰብ ነው እንጂ፡፡ በርግጥ ዛሬ ብዙ ችግር አለብን፡፡ ችግሩም የተፈጠረው በእኛው እንደመሆኑ ከችግሩ የመውጫ መንገዱ አንድነት ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ከአሉባልታ መጽዳት ይገባል፡፡”

82 ኛዉ የኢትዮጵያዉያን የድል በዓል ተከበረምስል፦ Seyoum Getu/DW

እለቱን የስታወሱ አርበኞችና የአርበናኛ ልጆች፤ እለቱን አስመልክተው በሰጡን አስተያየት የአርበኞች አልሸነፍ ባይነትና የአገር ፍቅር የዛሬን ኢትዮጵያ ለትውልድ ማቆየቱ አንድምታው ላቅ እንደሚል ይገልጻሉ፡፡ ትውልዱም በፈተና እዚህ የደረሰችን አገር ተረክቦ ኃላፊነቱን እንዲወጣ በአስተያየታቸው ጠይቀዋል፡፡

82 ኛዉ የኢትዮጵያዉያን የድል በዓል ተከበረምስል፦ Seyoum Getu/DW

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴም፤ ኢትዮጵያ ከእንግዲህ ደም የሚፈስባት ምድር መሆን እንደማይገባት፤ በመታሰቢያ በዓሉ ላይ ባስተላለፉበት መልእክታቸው ተናግረዋል፡፡ “ህቺ አገር ዳግሞ የልጆቻን ደም የምትጠጣ ማድረግ አይገባም፡፡ ስንተባበር ስንደማመት ነው ኢትዮጵያችን እያደገች ወደፊት የምትሄደው፡፡” 82ኛው የአርበኞች መታሰቢ በዓል ዛሬ ሲከበር ከባለስልጣናቱ እና አርበኞች በተጨማሪ ታዳጊዎች እና የተለያዩ የማህበረሰብ አካላትም ወጥተው እለቱን በድምቀት አስታውሰውታል፡፡

ሥዩም ጌቱ

አዜብ ታደሰ

ዮኃንስ ገብረግዚአብሔር

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW