dw.com: አዲስ ንድፍ፣ የተመለደ ይዘት
ማስታወቂያ
የዶቸ ቬለ ድረ-ገፅ በአዲስ መልክ በመሻሻሉ፣ መረጃና ይዘቶቻችንን የሚያገኙበት መንገድ ተቀይሯል።
በይዘት ላይ የተመሠረተዉ አዲሱ መፈለጊያ (ማሰሺያ) የዶቸ ቬለ መረጃዎችን በቀላሉና ለተጠቃሚ በሚስማማ መንገድ ለማግኘት የሚመች ነዉ።
ቤታ የተሰኘዉ አዲሱ ድረ-ገፅ ከተዘጋጀና ከተሞከረ በኋላ ነባሩ የዶቸ ቬለ ገፅ ይዘጋል፤ አዲሶቹ ገፆች ሙሉ በሙሉ ለተጠቃሚ ክፍት ይሆናሉ።
አዲሱ ምንድነዉ?
- ገፆቻችንን ለማግኘት የሚጠቀሙበት መሳሪያ (ስልክ፣ ታብሌት፣ ዴስክቶፕ ወዘተ) ምንም ሆነ ምን የገፆቻችን አወቃቀር ተመሳሳይ ነዉ።
- ገፆቻችን በተንቀሳቃሽ መሳሪያዎች፣ ማለት በስማርት ስልክና ታብሌት ለመታየት የሚመቹ ናቸዉ።
- ይዘቶቻችን (መረጃዎቻችን) ለዕይታ ማራኪ ናቸዉ።
- ይዘቶቹን (መረጃዎቹን) ያጠናቀሩትን ጋዜጠኞች ማንነት በቀላሉ ማወቅ ይችላሉ።
ይሕ በእንዲሕ እንዳለ፣ አዳዲሶቹን ገፆች ማዘጋጀትና ማዳበሩ ይቀጥላል።አዳዲስ፣ ምቹና ሳቢ ገፅታዎች እየተዘጋጁ ነዉ።