የአፍሪቃ የፊልም ፌስቲቫል ኦጋዱጉ
ረቡዕ፣ የካቲት 22 2009ማስታወቂያ
በዚህ የፊልም ሥራዎች ዉድድር ላይ ለመጨረሻዉ ምርጫ ከቀረቡት 20 ፊልሞች መካከልበአጭር ፊልሞች ዘርፍ የሚሳተፈዉ ባልደረባችን ማንተጋፍቶት ስለሺ ሥራ ግርታ የተሰኘዉ ፊልምም ተካቷል። ከእሱ ሌላም ፍሬ የተሰኘ ረዥም ፊልሙን ይዞ የቀረበዉ ክንፈ ማሞ በዚሁ ዉድድር በመሳተፍ ላይ ይገኛል። እስካሁን የደረሱበትን ዉጤት ለመገመት ቢከብዳቸዉም ፊልሞቻቸዉ በታዩባቸዉ የተለያዩ አዳራሾች ከተመልካች አበረታች ምላሽ ማግኘታቸዉን ሁለቱም ኢትዮጵያዉያን የፊልም አዘጋጆች ገልጸዉልናል። ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት ወደ ኦጋዱጉ ደዉዩ በአጭሩ አነጋግሬያቸዋለሁ። በቅድሚያ ያገኘሁት ባልደረባዬ ማንተጋቶትን ነዉ።
ሸዋዬ ለገሠ
አዜብ ታደሰ